የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በሰንጠረዥ የተገለፀውን ፍላጎት በሃገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈለጋል፡፡
ADDIS ABEBA CITY BUS SERVICE ENTERPRICE (የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት)
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አአከአአድ/ግጨ/ፅፅዳ/004/2017
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በሰንጠረዥ የተገለፀውን ፍላጎት በሃገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈለጋል፡፡
|
ተ.ቁ
|
የሚገዛው ዕቃ (አገልግሎት) አይነት
|
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን
|
የጨረታ ሰነድ መመለሻ ቀን
|
የጨረታ ሰነድ መክፈቻ ቀን
|
|
1 |
ሎት፡- የፅዳት ዕቃዎች
|
ብር 300,000.00
|
ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም ሰዓት 4:00
|
ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም ሰዓት 4:30
|
|
2 |
ሎት2፡-የጽሕፈት መሳሪያዎች
|
ብር 300,000.00
|
ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም ሰዓት 4:00
|
ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም ሰዓት 4:30
|
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡-
- ከስራው ጋር አግባብነት ያለው ሆኖ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የዘመኑ ግብር መክፈላቸውንና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ወቅታዊ ደብዳቤ (Tax Clearance) በአላይን የመንግስት ግዥ አቅራቢዎች ዝርዝር (https://www.egp.ppa.gov.et) ላይ የተመዘገቡ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (VAT Registration) እና የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት (TIN Certificate) ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ) በመያዝ 22 እየሩስ ህንፃ 7ኛ ፎቅ አዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-01 መውሰድ የሚችሉ ሆኖ የጨረታው ሰነድም በዚሁ አድራሻ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች በሰንጠረዡ በተገለፀው የብር መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ከህጋዊነት ማረጋገጫ /ከቴክኒካል/ ኦሪጅናል ሰነዶች ጋር በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማስያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከወሰዱበት ቀን ጀምሮ በተራ ቁጥር 2 በተገለፀው አድራሻ ከላይ በሰንጠረዥ በተገለፀው ቀን ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሰነዱ የሚከፈት ሲሆን ዘግይቶ የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዳቸው ሎቶች የታሸገ አራት ኤንቨሎፕ (ቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ) ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ ፓስታዎቹ ላይ መገለፅ አለበት፡፡
- የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የጠጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታውን የሚመለከት መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0118-21-22-14 በመደወል ማግኘት ይችላሉ::
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት
