በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን የቦረና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት አመት ከዚህ በታች በዝርዝር የተጠቀሱትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን የቦረና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን የቦረና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት አመት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ፡-
|
1. የፅህፈት መሳሪያ ሎት 1 2. የፅዳት ዕቃ ሎት 2 3. ኤሌክትሮኒክስ ሎት 3 4. የቢሮ ቋሚ እቃ /ፈርኒቸር/ ሎት 4 5. የስፓርት ትጥቅ ሎት 5 6. የእንስሳት መድሃኒት ሎት 6 7. ብትን ጨርቅ 6000 ቲትረን እና ሱፍ መሰል ጣቃ ሎት 7 8. አጭር ቆዳ ጫማ አጭር ቆዳ ቡትስ ጫማ ፕላስቲክ ቦት ጫማ ሎት 8 |
9. የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች ሎት 9 10. የተዘጋጁ ልብሶች ሎት 10 11. የመኪና ጎማ ሎት 11 12. ቋሚ እና አላቂ የቢሮ እቃዎች ሎት 13. የመኪና ስፔርፓርት ሎት 13 14. ህትመት ሎት 14
|
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- እግባብ ያለው በዘመኑ የታደሰ በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው!
- ግዢው ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- የሚገዙ ዕቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፤
- ተጫራች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 5 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሲፒኦ እና በጥሬው የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 1% እና ከዚያ በላይ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይንም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ግዢው በሎት የሚፈጸም መሆኑን አውቆ የእያንዳንዱን ዝርዝር እቃዎች ዋጋ መሙላት ይኖርበታል፤ ውድድሩ በሎት ዋጋ የሚካሄድ ነው፡፡ የተዘረዘሩትን እቃዎች በሙሉ ያለመሙላትና ስርዝ ድልዝ ያለው ማህተምና ፊርማ ያለማድረግ ከጨረታ ውጭ ያስደርጋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆነ በሁለት ቅጅ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቦ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 9 ግዥ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ደኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ በግዢ ከፍል ቢሮ ቁጥር 9 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቶች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የመጨረሻው ቀን በዓል እሁድ ወይም ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የመንግስት የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚዘጋና የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- የንብረት ርክክብ የሚፈፀመው ቦወ/ገንዘብ ጽ/ቤት እና ሴክተር መ/ቤቶች መሆኑ ይታወቅ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ከቢሮ ቁጥር 9 በቦ/ወ/ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በመገኘት ወይም በፋክስ ቀጥር- 0332200990 በመላከ ወይም በስልክ ቀጥር 0332205441/0938429553 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት
የደቡብ ወሎ ዞን የቦረና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
