በዋግ ኸ/ብ/አስ/ር ዞን በአምደወርቁ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም በጀት አመት ለከተማ አስተዳደሩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1፤ የጽህፈት መሳሪያዎች ሎት 2፤ ኤሌክትሮኒክስ ሎት 3፤ የጽዳት ዕቃዎች ፣ ሎት 4፤ የፈርኒቸር ዕቃዎች ሎት 5 ፤ የደንብ ልብስ ሎት 6፤ የእስፖርት ትጥቆች ሎት 7፤ የህንጻ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ወይም ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የዋግ ኸ/ብ/አስ/ር ዞን በአምደወርቁ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ 01/2017
በዋግ ኸ/ብ/አስ/ር ዞን በአምደወርቁ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም በጀት አመት ለከተማ አስተዳደሩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1፤ የጽህፈት መሳሪያዎች ሎት 2፤ ኤሌክትሮኒክስ ሎት 3፤ የጽዳት ዕቃዎች ፣ ሎት 4፤ የፈርኒቸር ዕቃዎች ሎት 5 ፤ የደንብ ልብስ ሎት 6፤ የእስፖርት ትጥቆች ሎት 7፤ የህንጻ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ወይም ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት፣
- የግዥ መጠኑ ከብር 200 000/ሁለት መቶ ሺህ በላይ ለሆነ ግዥ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፣
- የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያለው፣
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቺው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ( ቢድ ቦንድ ) የሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከተቋሙ ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ መሂ 1 ኮፒ ከፖስታው ጋር ማያያዝ አለባቸው፣
- የእቃዎቹን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን / ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመሰስ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር ብቻ/ ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት
- ከላይ በሎት የወጡት የጨረታ አይነቶች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን በስራ ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ የገዙትን ሰነድ አስገብተው 4:30 ይከፈታል፣
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን በዕለቱ ካልተገኙ መ/ቤቱ በሌሉበት የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመ/ቤቱ ግ/ፋ/ን/ አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ በጥንቃቄ ያልታሸገ ፖስታ ከውድድ ውጭ ይደርጋል።
- ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ካላደር ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ተመሳሳይ ቀን ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት እስከ አምደ ወርቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡ ከታዘዘው እስፔስፍኬሽን ውጪ ቢያቀርብ በራሱ ወጪ ዕቃውን ወስዶ ቀይሮ የማምጣት ግዴታ አለበት
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- ጨረታው ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም ፣
- በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህግና ደንቦች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በመ/ቤቱ ግ/ፋ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር /0914684377/0963677829/
በአብክመ በዋግ ኸ/ብ/አስ/ር ዞን የአምደወርቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት
