Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ሰርጢ ጤና ጣቢያ
  • Address አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በወረዳ 8 ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 36 75 67 74
  • Website
  • Deadline23 Oct 2024, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Others

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ሰርጢ ጤና ጣቢያ በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የደንብ ልብስ፣ ህትመት፣ የጽዳት ዕቃ፣ የህክምና እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የቤት ጥገና አገልግሎት እና ልዩ ልዩ እቃዎች ከህጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ሰርጢ ጤና ጣቢያ


የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ሰርጢ ጤና ጣቢያ በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የደንብ ልብስ፣ ህትመት፣ የጽዳት ዕቃ፣ የህክምና እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የቤት ጥገና አገልግሎት እና ልዩ ልዩ እቃዎች ከህጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ማሳሰቢያ፦

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው::
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ መሆን አለበት፡፡
  3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት እቃ ናሙና በእስፔስፊኬሽን መሰረት እና በእጃቸው ላይ የሚገኝ እንዲሁም በተጠየቁ ሰዓት ወዲያው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት የተቀመጠውን በባንከ በተረጋገጠ ዋስትና CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ ማስያዝ አለባቸው::
  5. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የጨረታው መመሪያ ሆኖ ችግሮች ካጋጠሙ በግዥው መመሪያ የሚዳኙ ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች የሞሉትን ሰነድ በፖስታ አሽገው ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ብለው በመፃፍ የድርጅታቸውን ማህተም ፊርማ በማድረግ ለዚሁ ተበሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  7. የውል ማስከበሪያ የግዥውን ግምታዊ ዋጋ 10% ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. የወሰዱትን ሰነድ ዋናዋና ቦታዎች ላይ በመፈረም ሙሉ ሰነዱን ተመላሽ ማድረግ አለባቸው፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ይሆንና በ11 ኛው ቀን 3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 412 ይከፈታል፡፡
  11. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው አስር የስራ ቀናት ተከታታይ ቢሮ ቁጥር 412 በመቅረብ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ሰነድ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  12. የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ወይም በካሽ መቅረብ ስላለበት ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት የጨረታ ማስከበሪያ እንድታሲዙ እያሳሰብን ለጨረታ ማስከበሪያ የምታቀርቡት (የምታሰሩት) (CPO) ወይም በካሽ ብቻ ማስያዝ እንዳለባችሁ እና የምታስይዙትን በየሎቱ በዝርዝር እንደሚከተለው አስቀምጠናል።

በመሆኑም፦

• 6211 -ደንብ ልብስ የሚወዳደር =100,000.00 ብር

• 6212 - አላቂ የቢሮ እቃዎች የሚወዳደር = 40,000.00 ብር

• 6213 - ህትመት የሚወዳደር 40,000.00 ብር

• 6214 - መድሀኒትና የህክምና እቃዎች የሚወዳደር =160,000.00 ብር

• 6218 - አላቂ የጽዳት እቃዎች የሚወዳደር =60,000.00 ብር

• 6219 - ልዩ ልዩ ዕቃዎች የሚወዳደር = 30,000.00 IC

• 6313 - ቋሚ እቃዎች የሚወዳደር =60,000.00 ብር

• 6244 - የቤት ጥገና የሚወዳደር =50,000.00 ብር

አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በወረዳ 8 ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 09 36 75 67 74

ከአንድ በላይ ጨረታ የወጡ መደቦች ላይ ዋጋ የሚሞላ ተጫራች የሞላውን እቃ ድምር ሁሉም ላይ የሞላ

ደግሞ የሁሉንም ድምር የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ

8 ሰርጢ ጤና ጣቢያ

 

Save Tender