የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አስተዳደር ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የአገልግሎት ግዥ ለ2017 በጀት ዓመት አወዳድሮ አገልግሎት ለመፈፀም ይፈልጋል።
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አስተዳደር
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2017
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አስተዳደር ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የአገልግሎት ግዥ ለ2017 በጀት ዓመት አወዳድሮ አገልግሎት ለመፈፀም ይፈልጋል።
ሎት 1 የህትመት ስራ አገልግሎት
ሎት 2 መኪና ኪራይ
ሎት 3 ዲኮር መድረክ እና ድንኳን ኪራይ
ሱት 4 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና
ሱት 5 የመኪና ጥገና
ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛሉ:: በዚህም መሰረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- አግባብነት ያለው የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የቫት ተመዝጋቢዎች የሆኑ:
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን በመገኘት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመከፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚጫረቱበት የጨረታ ሎት ዓይነት ህትመት 20,000 (ሀያ ሺ ብር) መኪና ኪራይ 50.000 (ሀምሳ ሺ ብር) ዲኮር መድረክ እና ድንኳን ኪራይ 30,000 (ሰላሳ ሺ ብር) ኤሌክትሮኒክስ ጥገና 10,000 (አስር ሺ ብር) መኪና ጥገና 50.000 (ሀምሳ ሺ ብር በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሰነድ የስራውን ዝርዝር የሚገልጽ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻ ዋናውን (ኦርጅናል) እና የማይከፈት ኮፒ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ስምና አድራሻ በመጥቀስ የድርጅቱ ማህተም ያረፈበትን ፖስታ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን 4፡30 ላይ ይከፈታል የጨረታው መክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ በማግስቱ ባለው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4:30 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡበት የነጠላ ዋጋ በሰነዱ ላይ በመግለጽ ሙሉ አድራሻና ማህተም መጠቀም አለባቸው::
- የተሻለ አማራጭ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ሙሉ አርጅናል የጨረታ ሰነድ ዋጋ ተሞልቶበት ህጋዊ ማህተም እና በየገጹ ፊርማ ተደርጎበት መመለስ አለበት ካልተመለሰ ከጨረታ የሚሰረዝ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ለህትመት ስራ ሳምፕል መቅረብ አለበት
አድራሻ ፡- ቤተል ከጊዮርጊስ ቤተከርስቲያን አጠገብ ያለው ህንጻ ላይ የአስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02
ስልክ ቁጥር 0118-34-09-79
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ
አስፈጻሚ ፑል
