ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ11 አስተዳደር ለሚ ቅድመ መደበኛ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በ2017ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር ጥቅል ግዥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ11 አስተዳደር ለሚ ቅድመ መደበኛ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ11 አስተዳደር ለሚ ቅድመ መደበኛ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በ2017ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር ጥቅል ግዥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2017ዓ.ም
|
|
የዕቃ ዝርዝር |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ |
|
ሎት1 |
የደንብ ልብስ |
7,500.00 |
|
ሎት2 |
አላቂ የቢሮ እቃ |
2,000.00 |
|
ሎት3 |
ህትመት |
2,500.00 |
|
ሎት4 |
የህክምና ዕቃዎች |
4000.00 |
|
ሎት5 |
አላቂ የትምህርት ዕቃዎች |
6,000.00 |
|
ሎት6 |
የፅዳት ዕቃ |
7,000.00 |
|
ሎት7 |
ልዩ ልዩ መሳሪያ ግዥ |
2,500.00 |
|
ሎት8 |
ለተገጣጣሚ እድሳት ጥገና |
4,500.00 |
|
ሎት9 |
ለፕላንት እና ለማሽነሪ ግዝ |
10,500.00 |
|
ሎት10 |
ለህንፃ ቁሳቁስ ለተገጣጣሚ መግዣ |
8,000.00 |
ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የተሰማራ ህጋዊ የ የሆነና የታደሰ የንግድ ፈቃድ እንዲሁም የግብር መለያ ቁጥር (TIN No) ሊኖራቸውና ሊያቀርቡ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል ፡፡
- ለሚያቀርቡት ዕቃ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ሊሆኑ ይገባቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ እና የተጫራቾች የምስከር ወረቀት ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 3 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ከላይ በተዘረዘሩት ሎት መሰረት ለእያንዳዳቸው የዋጋ ማስከበሪያ በተጠቀሰው ብር መጠን በባንክ በተረጋገጠ (ሲ ፒ.ኦ) ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00(አንድ መቶ ብር) በመክፈል በለሚ ቅድመ መደበኛ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ን/ አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ድረስ በመቅረብ መግዛትና መጫረት ይችላሉ
- ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ ኮፒ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ ብለው በመለየትና በ2 ፖስታ በማሸግ እንዲሁም የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው በለሚ ቅድመ መደበኛ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ውስጥ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በቀኑ ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
- በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ፡፡
- መስሪያ ቤቱ የሚገዛው ዕቃ ላይ 20% መጨመር እና መቀንስ ይችላል ::
- ከት/ቤቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0116 67 76 35 ወይም በአካል ለሚ ቅድመ መደበኛ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ሰሚት ኮንደሚኒየም 3ኛ በር ገባ ብሎ ቦሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 11 ትንሽ ወረድ ብሎ ፋይናንስ ግዥና ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል።
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ለሚ ቅድመ መደበኛ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
