አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ 001/2017 በጀት ዓመት የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የተለያዩ አላቂ እና ቋሚ የስልጠና እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች ፣ የደንብ ልብስ ፣የመኪና እቃዎች እና የመሳሰሉት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።
አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ 001/2017 በጀት ዓመት የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የተለያዩ አላቂ እና ቋሚ የስልጠና እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች ፣ የደንብ ልብስ ፣የመኪና እቃዎች እና የመሳሰሉት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- ተጫራቶች አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ግንፍሌ ኩዊንስ ኮሌጅ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ወረዳ 7 ጥቃቅንና አነስተኛ የሚገኘው ግቢ አራዳ ማነፋከቸሪንግ ኮሌጅ የግዥ ክፍል በመገኘት ኮሌጁ የተጠቀሱትን የተለያዩ እቃዎች የግልፅ ጨረታ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመወዳደር፡-
- በእቃው ወይም አገልግሎት አቅራቢነት በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ የተመዘገበ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- የንግድ ምዝገባ ፍቃድ የሚያቀርብ
- የዘመኑን የንግድ ፍቃድ ያሳደሰና ማስረጃው ግልፅ የሆነና የሚነበብ ኮፒ ማቅረብ የሚችል የዘርፉ ዓይነት በግልፅ የተቀመጠ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል።
- በጨረታ ለመሳተፍ በቅድሚያ
- ለሎት 1. ለሎት የስልጠና እቃዎች -----------ብር -----------10,000.00
- ለሎት 2 የቢሮ እቃዎች አላቂ እና ቋሚ ----------ብር-------- 5000.00
- ለሎት 3. የፅዳት እቃዎች----------ብር ----------5000.00
- ለሎት 4 ደንብ ልብስ -------------ብር----------5,000.00
- ለሎት 5 የመኪና እቃዎች----------ብር ---------3,000,00
- ለሎት 6. ህትመት ውጤቶች ----- ብር ---------2,000.00
- ለሎት 7 ለክሊኒከ እቃዎች ------- ብር --------- 3,000.00
- ለሎት 8. የውሃ------------ ብር -----------------1,000.00
-
- ለሎት 9. የካፍቴሪያ አገልግሎት አራዳ ማነፋክቸሪንግ ዋና ግቢ ----- 5000
- ሎት 10. የካፊቴሪያ አገልግሎት አዋሬ ካንፓስ ግቢ -----ብር ---- 5000
ለጨረታ ዋስትና የሚሆን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል፤ ያስያዙትም የጨረታ ዋስትና - ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ ጥቅምት ድረስ ከማወዳደርያ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በኮሌጁ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 57 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የግልፅ ጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የመወዳደርያ ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የመወዳደርያ ዋጋቸውን ኮሌጁ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ የአንዱን ዋጋ ቫትን ያካተተ ጠቅላላ ዋጋ የሚለውን በግልፅ ሞልቶ ኦርጅናል እና ኮፒ በሁለት ፖስታ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህን በግልጽ ሞልቶ ያላቀረበ ተጫራች ዋጋው ቫትን ያካተተ ነው ተብሎ ይወሰዳል።
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑበትን እቃ በራሳቸው ትራንስፖርት አውራጅ የጉልበት ሰራተኛ በመመደብ ለኮሌጁ ንብረት ግምጃ ቤት ያስረክባሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን እቃዎች በምርመራ ላይ በተቀመጠው ላይ መሆን አለበት።
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊ ድርጅቶች ጋር ከውል በፊት በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው የአቅርቦት መጠን ላይ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይቻላል።
አድራሻ፡- አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ግንፍሌ ኩዊንስ ኮሌጅ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ወረዳ ሰባት ጥቃቅንና አነስተኛ ሰርቶ ማሳያ ማእከል ግቢ ውስጥ
ጥብቅ ማሳሰቢያ፦ የጨረታ ሂደቱን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ለወደፊቱ በመንግስት ግዥ ላይ እንዳይሳተፉ ታግደው ያስያዙት ዋስትና ይወረሳል።
ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ለመሳተፍ በሰነዱ ምርመራ ላይ በተጠቀሰው መሰረት: ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው ለሚወዳደርበት እቃ ቅድሚያ ሳምፕል ወይም ደግሞ ናሙና ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለበት። ሳምፕሎችና ናሙናዎች ስድስት ወር ካለፋቸው ለተቋሙ ገቢ ይሆናሉ፡፡
በስፔስፊኬሽን ለሚጠየቁ እቃዎች በስፔስፊኬሽን መሰረት ካላመጡ ያስያዙት የውል ማስከበርያ ይወረሳል
ስልክ ቁጥር-01-11-26-18-26 እና 01-11-11-16-28
አራዳ ማኑፉክቸሪንግ ኮሌጅ
