የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፀውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር MSF/LP/10/2024
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፀውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
አንድ ጥቅል Roof Re-Construct Contractor as per the attached bid document pre- condition & Construction rules (የፋብሪካ ጣሪያ ግንባታ)
ጥቅል ሁለት፡- Chimeny re-construction Contractor as per the attached bid document pre- condition & construction rule (የቦይለር ቁጥር 4 ጭስ ማውጫ መልሶ ግንባታ)
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል ::
- ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፤የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች ለጥቅል አንድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) እንዲሁም ለጥቅል ሁለት ብር 300 (ሶስት መቶ) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሠዓት ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ህንፃ ግዥ ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 215 የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሲገዙ የንግድ ፈቃድ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሠነድ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ የአቅራቢዎች የምዝገባ ሠርተፍኬት እና ለጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ከ1.5 - 2% የሚሆን በሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ (Proforma invoice) ላይ በማዘጋጀት በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እ.ኢ.አ. ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ድረስ ሜክሲኮ ፊሊፕስ ሕንጻ ቢሮ ቁጥር 119 ማቅረብ ይኖርባቸዋል ::
- ጨረታው በዕለቱ ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 119 ውስጥ ተጫራቾች ወደም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ፡፡
- ፋብሪካው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ስልክ ቁጥር 0115-505607, 0115-505633
ሜክሲኮ አደባባደ ፊሊኘስ ሕንፃ
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ
