የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በ2017 በጀት ዓመት ለኤጀንሲው የሚያስፈልጉ የተለያዩ እቃዎች ሎት1፡- ግማሽ ሊትር የታሸገ ውሃ፣ ሎት 2፡- የተለያዩ የፕሪንተርና ፎቶ ኮፒ ቀለሞች፣ ሎት3፡- የኮምፒውተርና ተዛማጅ ዕቃዎች የጥገና አገልግሎት ፣ ሎት 4፡-የተለያዩ ሕትመቶች ሎት፡-5 ካሜራና ተያያዥ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ

ስለሆነም ተጫራቾች፤
- የዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፒያሳ ከጣይቱ ሆቴል ጀርባ ዋስትና የንግድ ማዕከል 6ኛ ፎቅ ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ሕጋዊ ስልጣን ያለውን አካል ፊርማ በማኖር በሰም በታሸገ ማህተም ያረፈበት ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ10ኛው የሥራ ቀን 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዋስትና የንግድ ማዕከል 5ኛ ፎቅ የግዥ፣ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። ነገር ግን 11ኛው ቀን በዓል ፣ ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 = ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም CPO ማስያዝ አለባቸው፡፡ እያንዳንዱ ተወዳዳሪ የቴክኒክና የፋይናንስ ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ሎት- 2 የተለያዩ የፕሪንተርና ፎቶ ኮፒ ቀለሞች ተጫራቾች ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0115336497
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ