የጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት በሶስት ሎት ማለትም ሎት 1 የሰመር-ሰብል ፓምፕ እና ኬብል ግዥ፣ ሎት 2. የራይዘር ፓይፕ ግዥ እና ሎት 3. የውኃ እቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር GTWSSS/0003/2017 E.C
የጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት በ ሶስት ሎት ማለትም ሎት 1 የሰመር-ሰብል ፓምፕ እና ኬብል ግዥ፣ ሎት 2. የራይዘር ፓይፕ ግዥ እና ሎት 3. የውኃ እቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መረጃዎች በማቅረብ በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡-
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- የግብር ከፋይነት ሰርቲፊኬት (TIN) ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ /NAT/ Register / የሆኑና
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለእያንዳንዱ ሎት የጠቅላላ ዋጋውን 1% ሲፒአ (Cpo) ብቻ ማስያዝ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመከፈል ጎንደር ከተማ ውኃና ፍሳሽ አገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 27 በመግዛት፤ በጨረታ ዝርዝሩ መሰረት ዋጋቸውን በመሙላትና በፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 14 ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የተወዳደሩበትን የጨረታ ዓይነት ተለያይቶ በታሸገ ፖስታ አንድ ኦሪጅናል (ቴከኒካልና ፋይናንሻል)፣ (አንድ ኮፒ (ቴከኒካልና ፋይናንሻል) የያዙ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ከ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ከጨረታ መክፈቻ ቦታ ላይ ካልተገኙ የጨረታ ኮሚቴው ጨረታውን የመከፈት መብት አለው፡፡
- የጨረታው መከፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል:: በአገር አቀፍ በዓላት ምክንያት ካልተዘጋ በስተቀር ዘወትር ቅዳሜ እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት የስራ ቀናት ሲሆን ይህም እንደ አንድ ሙሉ የስራ ቀን ይቆጠራል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 058-211-33-16 /058-112-06-97 በመደወል ማነጋገር ይችላሉ፡፡
በጎንደር ከተማ ውሃና ፍሣሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ግዥና
ንብረት አስተዳደር
