ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ኢማ የተለያዩ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች እና ጎማዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር Gada/NCB/04/2017
ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ኢማ የተለያዩ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች እና ጎማዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆንም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በዘርፉ የተሰማሩ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ እንዲሁም የንግድ ምዝገባ ምስክር እና ሌሎች አስፈላጊውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 በመምጣት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ከብ ማህተም በማድረግ እና በመፈረም በሰም በታሸገ ፓስታ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የሞሉትን ጨረታ ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት የዋጋውን ውል ማስከበሪያ 10 % በማስያዝ ውል መፈረም ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና ራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይችሉም
- በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰረዘ እና የተደለዘ ሆኖ ለመለየት የሚያስቸግር ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል እንደተፈጸመ ተመላሽ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 8፡30 ላይ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን
በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ :- ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-558-25-19
ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አ.ማ
