በደ/ኢ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጎፋ ዞን ሣውላ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የውሃ ቧንቧና፣ መገጣጠሚያዎች፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሳውላ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ኢ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጎፋ ዞን ሣውላ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ
ሎት-1 የውሃ ቧንቧና፣ መገጣጠሚያዎች (ስድርጅቱ የውሃ መስመር ጥገና)
ሎት-2 የውሃ ቧንቧና፣ መገጣጠሚያዎች፣ ቆጣሪዎችና ሴሎች የውሃ ዕቃዎችን (ስሱቅ ሽያጭ)
ሎት-3 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን
ሎት-4 አላቂ የቢሮ ጽዳት ዕቃዎች
ሎት-5 የጽህፈት መሣሪያ
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት፡-
በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መረጃዎች አሟልታችሁ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
የሚፈለጉ መረጃዎች፡-
1. የታደሰ ንግድ ፍቃድ
2. በዘርፉ የተመዘገቡበት ህጋዊ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት
3. የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማረጋገጫ
4. TIN No /የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/
5. የVAT ተመዝጋቢነት ማረጋገጫ
6. የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት
7. የጨረታ ማስከበሪያ 25.000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ ሲፒኦ እና
8. ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነዶችን ኦርጅናል ብቻ በአንድ ፖስታ ማሸግ ይኖርባቸዋል ::
ማሳሰቢያ፡-
ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 60 ቀናት ሲሆን ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው :: የጨረታው አሸናፊው በጨረታው ያሸነፈውን ዕቃ/ንብረት እስከ ድርጅቱ ድረስ በራሱ የትራንስፖርት ወጪውን ሸፍኖ የሚያቀርብ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሠነድ ሽያጭ የሚከናወንበት በሣውላ ከተማ ውሃ አገ/ት ድርጅት ሲሆን ጨረታው በ 14/02/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ላይ ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል ፡፡
ለበለጠ መረጃ
በስልክ ቁጥር ፡- 0467770636፤0467770067፤0916387676፤ 0912913677 እና 0924027461 ደውላችሁ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
የሳውላ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት
