የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የተለያዩ ቋሚና አላቂ የላብራቶሪ መሳሪያ ዕቃዎች አገልግሎት ግዥ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Addis Ababa City Roads Authority (የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አአከመባ /ግብዓት/ ቡ-2/016/2017
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የተለያዩ ቋሚና አላቂ የላብራቶሪ መሳሪያ ዕቃዎች አገልግሎት ግዥ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
የጨረታ መለያ ቁጥር |
የጨረታ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ |
የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
ማስከበሪያ መጠን |
|
1 |
የተለያዩ ቋሚና አላቂ የላብራቶሪ መሳሪያ ዕቃዎች |
አአከመባ መደበኛ መሳሪያ /ቡ-2/016/2017 |
60 ቀን |
ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት |
ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት |
200,000.00 |
|
ጠቅላላ ድምር /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ |
200,000.00 |
|||||
ስለሆነም ፡-
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ በመስኩ የተሰማሩበት የንግድ ስራ ፍቃድ፣ታክስ ከሊራንስ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ድረ-ገፅ ላይ (Online PPA Supplier list Registration Certificate) መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚዘጋበት ጊዜ ድረስ ባሉት የስራ ቀናት ከባለስልጣኑ መ/ቤት የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 135 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንከ የቀረበ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የተለያዩ ቋሚና አላቂ የላብራቶሪ መሳሪያ ዕቃዎች አገልግሎት የሚሳተፉ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በሰንጠረዥ በተገለፀው መሰረት ሲሆን፤ የሚወዳደሩ ተጫራቾች 200,00.00(ሁለት መቶ ሺህ ብር) ማቅረብ ይችላሉ ከባንከ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከ ተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለስልጣኑ መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ድረስ ብቻ በባለስልጣኑ መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡
ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- ሳር ቤት ፑሽኪን አደባባይ
ስልክ ቁጥር ፡- 011-3-722825
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን
