ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ ለምርት ማሸጊያ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ማሸጊያ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡-APPF/02/17
- ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፓሬሽን የአዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ ለምርት ማሸጊያ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ማሽጊያ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ።
1.1. Different Adhesive Sticker Labels, Different Carton Labels, Different Carton Boxes, Glue, Printing ribbon.
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀትና ከገቢዎችና ጉምሩክ ሚኒስቴር በጨረታ እንዲሳተፉ የተጻፈላቸው የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች አዳሚ ቱሉ ባለው የፋብሪካው ዋና መስሪያ ቤት ወይም አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ከኩዌት ኢምባሲ 10 ሜትር ገባ ብሎ ጅቡቲ ኢምባሲ ፊት ለፊት ከሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ የማይመለስ ብር አምስት መቶ ብቻ (500.00) በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራች ድርጅት ስምና አድራሻ በትክክል ተፅፎ የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዶቻቸውን ኮፒ እና ኦሪጅናሉን በተለያየ በደም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በተጫራቹ ድርጅት ኃላፊ ተፈርሞና ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በአዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ ስም የባንክ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታው በቴክኒካል ሰነድ ጋር ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነዱን እስከ ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የፋብሪካ ዋና መስሪያ ቤት ወይም አዲስ አበባ በሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡የጨረታ መክፈቻው ዕለት ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ በሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ ይሆናል፡፡
- ፋብሪካው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- አ.አ ማስተባበሪያ
ስልክ ቁጥር 011-6-62-46-56/ አዳሚ ቱሉ 0416-4-41-91-64 (ማዞሪያ) 046-8-41-04-47 (ንግድ መምሪያ) ፖሣቁ 1206 (አ.አ) 247 (አ/ቱሉ)
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዳሚ ቱሉ
የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ
