በሀገር መከላከያ ሚ/ር የምስራቅ ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ ለ2017 በጀት ዓመት ለዕዙ አገልግሎት የሚውሉ የቀላል እና ከባድ ተሸከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች ፣ የጀኔሬተር እና የዳቦ ማሽን መለዋወጫ ዕቃዎች፣የወታደራዊ ተሽከርካሪ አላቂ መሥሪያ ዕቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የምስራቅ ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ ግዥ ዴስክ ሐረር
የጨረታ ማስታወቂያ
የምስራቅ ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ የግልጽ ጨረታ ቁጥር 01/2017 ዓ.ም
በሀገር መከላከያ ሚ/ር የምስራቅ ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ ለ2017 በጀት ዓመት ለዕዙ አገልግሎት የሚውሉ
1. የቀላል እና ከባድ ተሸከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች
2. የጀኔሬተር እና የዳቦ ማሽን መለዋወጫ ዕቃዎች
3. የወታደራዊ ተሽከርካሪ አላቂ መሥሪያ ዕቃዎች
በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ጨረታውን መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ በዚህ መሠረት በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ሠርተፊኬት ያላቸው፣ የምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመከፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ ከ2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት እና ከ7፡30 እስከ ከ፡ 11፡00 ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሐረር ምስራቅ ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ በሚገኘው ግዥ ዴስከ ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ። ጨረታው ጥቅምት 09 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:15 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐረር ቀላዳንባ በሚገኘው ሜንቴናንስ መምሪያ ግቢ ይከፈታል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር-0920437143/0913971279
በአገር መከሳከያ ሚኒስቴር
የምስራቅ ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ ግዥ ሐረር
