Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን
  • Address , Phone: 00 00 00 00
  • Website
  • Deadline12 Oct 2024, 11:26 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Others

በኢትዯጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በቅ/ፅ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢያዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተር ሳይክል እና የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ አልባሳት ዕቃዎች፣ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሞባይል ቀፎዎች ፣ ኮስሞቲክስ እና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች ፣ የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች ፣ ሞተር ሳይክሎች ፣ ብዛት 64 ካርቶን እያንዳንዱ ካርቶን በቁጥር 10,000 ቆርኪ (CROWN CORK)፣ መኪና እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች በግልፅ እና በሃራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል ።

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን


የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 03/2017

 

በኢትዯጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በቅ/ፅ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢያዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተር ሳይክል እና የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ አልባሳት ዕቃዎች፣ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሞባይል ቀፎዎች ፣ ኮስሞቲክስ እና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች ፣ የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች ፣ ሞተር ሳይክሎች ፣ ብዛት 64 ካርቶን እያንዳንዱ ካርቶን በቁጥር 10,000 ቆርኪ (CROWN CORK)፣ መኪና እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች በግልፅ እና በሃራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል ። በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን ።

    1. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃዎች ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያያዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል ።
    2. ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 – 12፡00 ሰዓት ቅዳሜ ከጠዋት 2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በፅ/ቤታችን የእለት ገቢ ገንዘብ ሰብሳቢ ቢሮ ቁ.ር 16 በመገኘት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ መዝጊያው ቀን ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ ።
    3. በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) እንዲሁም በሃራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ የመግዣ ዋጋ አምስት (5%) በጉምሩክ ኮሚሽን በሞያሌ ቅርንጫፍ ስም በኢትዯጵያ ንግድ ባንክ ማስያዝ ይኖርባቸዋል ።
    4. ጨረታው የሚካሄደው በሞያሌ ቅ/ፅ/ቤት ሲሆን ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ባሉበት ወይም ታዛቢ ፊት ይከፈታል ።
    5. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እስከ 7ተኛው ቀን ድረስ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ናሙና በሞያሌ እና በሁሉም መ/ጣቢያ የሚገኘዑ መጋዘኖቻችን እየሄዱ መመልከት አለባቸው ።
    6. ጨረታው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 3፡45 (ሶስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ) ተዘግቶ 4፡00 (አራት ሰዓት) ላይ ይከፈታል ።
    7. ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለፀው ጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 8ኛው ቀን የስራ ቀን ሳይሆን ቢቀር የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
    8. ለጨረታው አሸናፊ ተጫሮቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል ።
    9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል ።
    10. ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት CPO ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል ።
    11. ፅ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።  

        ለተጨማሪ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 0464441415/0464441564 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ ።

 

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት

Save Tender