Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ (Sidama National Regional Government Government Communication Affairs)
  • Address ሀዋሳ ከተማ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር ቢሮ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 418 : ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251916866043
  • Websitehttps://www.sidamanrsps.gov.et/
  • Deadline15 Oct 2024, 4:41 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Materials

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለ2017 በጀት ዓመት ለመሥሪያ ቤቱ የሚያስፈልጉ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የጽሕፈት መሣሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎችን ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ (Sidama National Regional Government Government Communication Affairs)


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለ2017 በጀት ዓመት ለመሥሪያ ቤቱ የሚያስፈልጉ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የጽሕፈት መሣሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎችን ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፦

  • ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምዝገባ ወረቀት፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆነው የጊዜ ገደብ የሚገልጽ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማስረጃ በመያዝ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል ሰነድ በመግዛት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የሥራ ቀናት ውስጥ በመቅረብ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  • ሰነድ የሚሸጥበት ቦታው በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 418 ነው::
  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ የውል ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በሕጋዊ ባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ በማዘጋጀት ኦሪጅናልና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከጨረታ መመሪያ ጋር አባሪ ተደርጎ ተያይዟል፡፡
  • ተጫራቾች መመሪያ ባለማከበራቸው የሚፈፀም ማንኛውም ስህተት ኃላፊነቱ የተጫራቾች ይሆናል።
  • ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣ በ፬ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡ 30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 10ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ የጨረታ መክፈቻው ዕለት በተጠቀሰው ሰዓት በሚቀጥለው ሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  • አቅራቢዎቹ የእቃ ዝርዝር ማቅረቢያ ፎርም ላይ ነጠላ ዋጋውን እና ጠቅላላ ዋጋውን እንዲሁም ቀን፣ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም ማሳረፍ ይገባቸዋል፡፡ አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  • አቅራቢዎች ጠቅላላ ዋጋ በቁጥርና በፊደል መጻፍ አለባቸው:: በቁጥርና በፊደል በተገለጸው የዋጋ መጠን መካከል አለመመጣጠን ካለ በፊደል የተገለጸው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ ነጠላ ዋጋ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
  • ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ ፡- በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር ቢሮ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 418

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት

የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

Save Tender