በአዲስ አበባ ቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ቂሊንጦ ለስራ አገልግሎት የሚውል ልዩ ልዩ የጥገና እቃዎችን ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል፡፡
የአዲስ አበባ ቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ቂሊንጦ
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ቂሊንጦ ለስራ አገልግሎት የሚውል ልዩ ልዩ የጥገና እቃዎችን ናስትሮ፣ ባለ 2.5 ኤሌከትሪክ ገመድ፣ ባለ 4 ኤሌክትሪክ ገመድ፣ ባለ 36ዋት ፍሎረሰንት አምፖል፤ ባለ 36ዋት ሆልደር፣ ባለ18ዋት ሆልደር፣ ባለ18ዋት አንፖል፣ ሪዚስታንት ባለo9፤ ሪዚስታንት ባለo8፤ ብሬከር ባለ 25 ኢንች፣ ፖውዛ አንፖል 1500ዋት፣ ፖውዛ ባለ 200ዋት ሲልድ፣ የእጅ ጓንት፣ ድጅታል ቴስት ላይት፣ ቡርሽ14x14፣እርሎ ቡርሽ፣ ሜትር ባለ 7፡50፣ ሲባጎ ገመድ ባለ4 ቲክነስ፤ ቶርኖ ማጠፊያ ትልቁ፤ የመበየጃ ፒንሳ፣ የበያጅ መነፅር፣ ማሰከሪያ፤ ኤሌክትሮድ ፐርማነንት 2.5፣ ሚስማር ባለ 4 ቁጥር፣ ሚስማር ባለ9 ቁጥር ሚስማር ባለቁጥር 10፤ ሚስማር ባለ ቁጥር 12 የቆርቆሮ ሚስማር አጭሯ፣ የድግን መጋዝ ምላጭ መቶ አለቃ፤ ታፕ የብረት 1/2 ታፕ የብረት 3/4፤ ሬዲውሰር የብረት 3/4-1/2፤ ሩቪነቶ ጎማኒ፣ የብረት ሶኬት 1/2፣ የብረት ሶኬት 3/4፣ የብረት ኤልቦ 1/2፤ ኒብልስ የብረት 1/2፤ ኒብልስ የብረት 3/4፤ ምጣድ ባለ 58 ስፋት፣ ጄሶ የምጣድ፣ ሶኬት ተንጠልጣይ፣ ኮኔክተር 150AM፤ ማብሪያ ማጥፊያ ተንጠልጣይ፣ ሬቬኔቶ 1/2፣ ሬቬኔቶ 3/4፤ ጌት ቫልቭ 1/2፤ ጌት ቫልቭ 3/4፤ ፊሜል ኤልቦ 1/2፤ ፊሜል ኤልቦ 3/4 ፤ ሜል አዳፕተር 1/2፣ ሜል አዳፕተር 3/4፤ ፊሜል አዳፕተር 1/2፤ፊሜል አዳፕተር 3/4 ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል፡፡
በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መመሪያና መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው የተገለፀ መሆን አለበት፡፡
- የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈለ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
- የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
- የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል አቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው
- ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ ከአደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 150.00/ አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ስም በአካውንት ቁጥር 1000007971347 ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 25 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ቴከኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን ፋይናንሻል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለበት። ቴከኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ በአንድ ላይ አሽጎ ያቀረበ ተወዳዳሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ውጭ ይደረጋል።
- ማንኛውም ተጫራቾች የሚያስገቡት ሰነድ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ እንዲሁም ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ በተለያዩ ፖስታ በማሸማ በፖስታው ላይ የሚጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ ቁጥር በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ እና በሁሉም የመጫረቻ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያስይዙት ሲፒኦ ከቴከኒክ ሰነዶች ከአርጅናሉ ጋር በአንድ ላይ አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00/ ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO በቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ሥም አዘጋጅተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ እስከ ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው እንዲሁም የባንክ ዋስትና የሚያስይዙ ተጫራቾች የቆይታ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 90 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል።
- ጨረታው ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5.00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቂሊንጦ በሚገኘው በመ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል።
- የጨረታው ዝርዝር መመሪያ በጨረታ ሰነዱ ተዘርዝሮ ቀርቧል፡
- አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም እንዲሁም ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም::
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ጨረታው በሚከፈትበት ቀን የዓመት በዓላት ከሆነና በተለያዩ ምክንያት ዝግ ከሆነ ጨረታው በሁለተኛው ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
አድራሻ ፡- ቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር አ/አ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ
ለበለጠ መረጃ +- 011 4 71 63 33 01/ 18 88 60 89/011 434 89 86 ደውለው መጠየቅ ይቻላል
በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር
