በድሬዳዋ አስ/ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት አዲስና ያገለገሉ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Dire Dawa Administration Public Procurement and Property Disposal Service (የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግሥት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በድሬዳዋ አስ/ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት ቀጥሎ በሰንጠረዡ የተመለከቱትን አዲስና ያገለገሉ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
|
ተቁ |
የንብረቱ ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
የዕቃዎቹ ሁኔታና የሚገኝበት ቦታ |
|
1 |
PEUGEOT አውቶሞቢል ያገለገሉ ፡- በአገር ውስጥ የተገጠሙ (ሞዴል 2008) |
በቁጥር
|
2 |
ድሬደዋ በድሬደዋ ደወሌ ም/ባቡር ድርጅትግቢ |
|
2 |
ልዩ ልዩ ዓይነት ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች |
በቁጥር |
6 |
“ ” |
|
3 |
SHS 25 *25* 3mm እና *60*60 *2.5mm |
በቁጥር |
1423 |
አዲስ /ያላገለገሉ/ የግንባታ ዕቃዎች ሆነው ከአስተዳደሩ ሲቪክ ሴንተር ፕሮጀክት ግንባታ ሳይት ከግንባታው ተርፈው በድሬደዋ ከተማ በድሬደዋ -ደወሌ ም/ባቡር ግቢ የሚገኙ |
|
4 |
Angle iron 50*3mm, 25* 1.5mm እና 25 *1mm |
በቁጥር |
180 |
|
|
5 |
RHS 40 *80 *2,5mm |
በቁጥር |
59 |
|
|
6 |
T-iron 30*3mm & L- profile 38 *1.25mm |
በቁጥር |
25 |
|
|
7 |
Fiato iron *40mm*3mm & 40*2mm |
በቁጥር |
82 |
|
|
8 |
Flexible Condit, rigid Condit & PVC Condit |
በቁጥር |
1262 |
|
|
9 |
Aluminum door & window frame |
በቁጥር |
241 |
|
|
10 |
Aluminum profiles with different shapes |
በቁጥር |
186 |
|
|
11 |
used Ega tin sheet 6meter |
በቁጥር |
40 |
|
|
12 |
used Metal & Plastic barrel |
በቁጥር |
30 |
አሮጌ /ያገለገሉ/ የግንባታ ዕቃዎች ሆነው በጥቅል ከአስተዳደሩ ሲቪክ ሴንተር ፕሮጀክት ግንባታ ሳይት ከግንባታው ተርፈው በጥቅል በድሬደዋ ከተማ በድሬደዋ ደወሌ ም/ ባቡር ግቢ የሚገኙ |
|
13 |
used steel formwork (panel) with different size |
በቁጥር |
282 |
|
|
14 |
scrap aluminum metal |
ባለበት |
በጥቅል |
|
|
15 |
galvanized rectangular central conditioning steel duct with different size & others galvanized metal |
ባለበት |
በጥቅል
|
|
|
16 |
galvanized steel scaffolding |
ባለበት |
በጥቅል |
|
|
17 |
ልዩ ልዩ ያገለገሉ ብረት ነክ ዕቃዎችና ሌሎች ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች (Scrap metal) |
ኪ.ግ.
|
ተመዝኖ |
ከአስተዳደሩ ድል ጮራ ሪፈራል ሆል፣ ከፐብሊከ ሰርቪስ ቢሮና ከስፖርት ኮሚሽን ወደ ድሬደዋ-ደወሌ ም/ባቡር ግቢ የገቡ |
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በድሬደዋ አስ/ ፋይናንስና ኢ/ል/ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 204 በመምጣት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት ማለትም ከመስከረም 22/2017 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም 11፡00 ሰዓት ድረስ የዕቃዎቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ለሽያጭ የተዘጋጁትን ንብረቶች ከመስከረም 22/2017 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 11/ 2017 ዓ.ም ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ከ3፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ድሬደዋ ከተማ በሚገኘው በድሬደዋ ደወሌ ም/ባቡር ድርጅት ግቢ በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ንብረት ለጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለፀውን የብር መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በድሬደዋ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት በመምረጥ የሚገዙበትን ዋጋ በአኃዝና በፊደል ለይተው ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ጽፈው ከፈረሙ በኋላ በኤንቬሎፕ አሽገው በአስተዳደሩ የግዥና ንብረት ማስወገድ አገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 204 በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ከመስከረም 22/2017 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ በ 4፡15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት ማስወገድ አገ/ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 204 ውስጥ ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ ከጨረታው መውጣት ወይም የሰጠውን ዋጋ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም፡፡
- የጨረታ መገምገሚያ መስፈርት ከፍተኛ ዋጋ እና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ ናቸው ፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ 7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፣
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ዕቃውን በ 10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣
- ለተሽከርካሪዎች ቀደም ሲል ያልተከፈለ የቦሎ፣ የስም ማዛወሪያ፣ የትራንዚት እና ሌሎች ወጪዎች በገዢው /በአሸናፊው ተጫራች ይሸፈናል፡፡
- ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ:- በስልክ ቁጥር 025 411 0164/09 12 273 839 በመደወል ወይም ንብረት ማስወገድ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁጥር 204 በመምጣት ተገቢውን መረጃ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት
