የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል በእንጨትና ብረታ ብረት፤ በትምህርትና ስልጠና ስራዎች አገልግሎት የሚውል የጥሬ ዕቃ ግብዓቶች፣ የጥገና፣ የቧንቧ፤ የመሰረተ ልማት፤ የሌሌክትሪክና የግንባታ ዕቃዎች አገልግሎት፣ የፅዳት፤ የምግብ ቤት እቃዎች እና የእንስሳት መኖ በግልፅ ጨረታ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል
የጨረታ ማስታወቂያ
የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፤
- ጨረታ ቁጥር (1) በእንጨትና ብረታ ብረት፤ በትምህርትና ስልጠና ስራዎች አገልግሎት የሚውል የጥሬ ዕቃ ግብዓቶች፣ የጨረታ ቁጥር (2) የጥገና፣ የቧንቧ፤ የመሰረተ ልማት፤ የኤሌክትሪክና የግንባታ ዕቃዎች አገልግሎት፤
- ጨረታ ቁጥር (3) የፅዳት፤ የምግብ ቤት እቃዎች እና የእንስሳት መኖ በግልፅ ጨረታ በጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት -
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ፤ በሥራው መስክ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በዕቃ ግዢና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ እና መለያ ቁጥር (Tin Number) ተመዝጋቢ የሆኑና የተሟላ ማስረጃ በ4 ኮፒ በማድረግ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን አንዱን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሰነድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000007971188 ገንዘቡን ገቢ በማድረግ አባሳሙኤል ማረሚያ ማዕከል ግዥ ከንውን ቡድን 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ ማ/ቤቱ የሚገዛቸው ዕቃዎች ዝርዝር በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ተዘርዝሮ ቀርቧል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ በጨረታ ቁጥር 1-3 ለተጠቀሱት ጨረታዎች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚመለስ ለእያንዳንዳቸው ብር 10,000.00 (አሥር ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች አንዱ በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ናሙና እንዲያቀርብ የተጠየቀባቸው ናሙናውን በጨረታ መክፈቻ ቀን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሠነድ መግዛትና የመወመዳደሪያ ሃሳባቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ቁጥር 1 ጥቀምት 4 ቀን 2017 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዳቸውን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዕለቱ በ4፡15 ሰዓት በማረ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ቁጥር 2 እና 3 ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ቁጥር 2 በዕለቱ በ4፡15 ሰዓት የጨረታ ቁጥር 3 በ5:30 ሰዓት በማረ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት እንዳስፈላጊነቱ ቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል (አባ ሳሙኤል አዲሱ ማረሚያ ማዕከል) በሚገኘው ዕቃ ግ/ቤት በአንድ ጊዜ አምጥተው ያስረከባሉ፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደረያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ማረሚያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ፕሮፎርማቸው ላይ ዋጋ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ የሌለበት ጎላ ብሎ የሚነበብ ፅሑፍ መሆን ይገባቸዋል፤ ስርዝ ድልዝ ያለበት ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡ በአሃዝና በፊደል መፃፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ቃሊቲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000007971188 አ/አ ማረ/ቤት ዕደ-ጥበባት ማዕከል በሚል ገንዘቡን ገቢ ካደረጉ በኋላ መግዛት ይችላሉ።
አድራሻ፡- አባ ሳሙአል ማረሚያ ማዕከል
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር -011- 4-39-76-61 ወይም 011-8-88-9181
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል
