በደ/ምዕ/ኢ/ክ/መ/በካፋ ዞን ጌሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለወረዳ ማዕከል ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገ/ት የሚውሉ የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ አላቂ ዕቃዎችና ተዛማጅ የጽዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ ጀነሬተር እና ሞተር ሳይክል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የደ/ምዕ/ኢ/ክ/መ/በካፋ ዞን ጌሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ምዕ/ኢ/ክ/መ/በካፋ ዞን ጌሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለወረዳ ማዕከል ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገ/ት የሚውል የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን ከህጋዊ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፤
1. ሎት 01 የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ አላቂ ዕቃዎችና ተዛማጅ የጽዳት ዕቃዎች፤
2. ሎት 02 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤
3. ሎት 03 የቢሮ ፈርኒቸሮች፣
4. ሎት 04 ጀነሬተር፤
5. ሎት 05 ሞተር ሳይክል፤
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
1. የዘመኑን ግብር በመክፈል የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድና ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፤
2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፤
3. ህጋዊ አቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
4. ከሚያገኘው ገቢ 2 በመቶ ገቢ የሚከፍል (ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ) መሆን ይኖርባቸዋል፤ ስለዚህ ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት 200 ብር በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ቀናት ጌሻ ወረዳ ገቢዎች ን/ቅ/ጽ/ቤት የቢሮ ቁጥር 34 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ጌሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ስም:
- ሎት 01 የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎችና አላቂ ዕቃዎችና ተዛማጅ የጽዳት ዕቃዎች 20,000 ብር
- ሎት 02 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና ተዛማጅ ዕቃዎች፣ 30,000 ብር
- ሎት 03 የቢሮ ፈርኒቸሮች 10,000 ብር
- ሎት 04 ጀነሬተር 10,000 ብር
- ሎት 05 ሞተር ሳይክል 10,000 ብር ከጨረታው ቴክኒካል ዶክሜንት ጋር በማዘጋጀት አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በየሎት በማከፋፈል እና የሎት ቁጥርን ሰነድ ላይ በመፃፍ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በዕቃው አይነት በታሸገ ኤንቨሎፕ የድርጅቱን ስም፣ ማህተምና ስልክ ቁጥር በመፃፍ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ቀናት ቆይቶ በ21ኛው ቀን እስከ 3፡00 ሰዓት ድረስ በጌሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ስራ ክፍል የቢሮ ቁጥር 03 በመቅረብ ለዚሁ ስራ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ተጫራቹ ድርጅት አሸናፊ መሆኑ ሲረጋገጥ ውል ሲገቡ የውል ማስከበሪያ 10% ለማስያዝ ፈቃደኛ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
የጨረታው ዋጋ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከተከፈተበት ጊዜ አንስቶ ለሰማኒያ ቀናት ይሆናል፡፡
ተጫራቹ አሸናፊ መሆኑ ሲረጋገጥ ወዲያውኑ ውል ገብቶ ዕቃዎችን በራሱ ወጪ እስከ ጌሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት አቅርቦ ያስረክባል።
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ስራ ክፍል በ21ኛው ቀን 3:30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት ጨረታውን አያስተጓጉልም::
ጨረታው የሚዘጋበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን በሰንበት ወይም በበዓል ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ተላልፎ ጨረታው ይከፈታል፡፡
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በደ/ምዕ/ኢ/ክ/መ/በካፋ ዞን ጌሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ ጽ/ቤት
