Tender Detail

Tender Details

  • Deadline30 Oct 2024, 12:16 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cloth And Shoes

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለበረራ አገልግሎት የሚውል ፒጃማ እና ስሊፐር የሚያቀርቡ አምራች ድርጅቶችን አወዳድሮ የረጅም ጊዜ ውል በመግባት አብሮ መስራት ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር :- SSNT-T492

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለበረራ አገልግሎት የሚውል ፒጃማ እና ስሊፐር የሚያቀርቡ አምራች ድርጅቶችን አወዳድሮ የረጅም ጊዜ ውል በመግባት አብሮ መስራት ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ ።

  1. የፒጃማ እና ስሊፐር የሃገር ውስጥ አምራች የሆነ ፤
  2. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው ፤ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፍቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነፃ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ እና በዘርፉ ሁለት (2) ዓመት እና ከዛ በላይ የስራ ልምድ ያላቸው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T492 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ የጨረታ ቁጥሩን ፣ የድርጅታቸውን ስምና ስልከ ቁጥር ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) "በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ” ስም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጨረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴከኒካል ክፍል እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ ∶- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

አቶ ተሰማ ሀብቴ

ስልክ ቁጥር፡- 011-5-17-42-58

ኢ-ሜይል :- TessemaH@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

Save Tender