በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል Different Normal Plate 1-Beams, U-Channels and Angle Irons በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሀገር ውስጥ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ሙሲፋ/Re-84/2016
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል Different Normal Plate 1-Beams, U-Channels and Angle Irons በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው (የ2016 ዓ/ም)፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጠቀሱትን ኮፒ ሰነዶች በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100.00 ከቫት በፊት በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ስም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (C.P.O) በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን
ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
ስልክ 0114420216 / ፋክስ 0114420688
አዲስ አበባ
