በአማራ ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ/ዞን/ የእንሳሮ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2017 በጀት አመት ከመደበኛ በጀት ላይ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎችን ለመግዛትና ለማሰራት እንዲሁም ለማስጠገን ስለሚፈለግ በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መመዘኛዎችን የሚያሟሉና በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ዘዴ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የአማራ ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ/ዞን/ የእንሳሮ ወረዳ ፍ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር /282/2017 ዓ.ም
በአማራ ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ/ዞን/ የእንሳሮ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2017 በጀት አመት ከመደበኛ በጀት ላይ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎችን ለመግዛትና ለማሰራት እንዲሁም ለማስጠገን ስለሚፈለግ በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መመዘኛዎችን የሚያሟሉና በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ዘዴ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት1. የጽሕፈት መሳሪያ እቃዎች/የኮምፒውተር ቀለሞች እና የአላቂነት ባህሪ ያላቸው እቃዎች
ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
ሎት 3 ቋሚ እቃዎች/ፈርኒቸር
ሎት 4 የጽዳት እቃዎች
ሎት 5 የህትመት ስራዎች
ሎት 6 የተዘጋጁ ልብሶች ብትን ጨርቅ/ጫማዎች
ሎት 7 ቋሚ እቃዎች ጥገና
ሎት 8 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገናዎች
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው::
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው::
3. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. የግዢው መጠን ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታከስ/ VAT
ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
5. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50/ሃምሳ ብር ብቻ/ በመከፈል
ጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ከግ/ፋ/ን/ አስ/ቡድን/የስ/ሂደት
ቢ.ቁ 03 በመቅረብ ዘወትር በስራ ሰአት መውሰድ ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች ለግዥው አይነትም ሆነ መጠን በጨረታው ሙሉ ለሙሉ መሙላት አለባቸው ማለትም
ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ሎት በሙሉ የተዘረዘሩትን እቃዎች መሙላት አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት በጨረታው ለመሳተፍ
ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መስሪያቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውንና ደጋፊ ማስረጃዎችን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ አማርኛ መሆን አለበት
9. መ/ቤቱ የአቃዎችን ናሙና የሚፈልጉ ከሆነ ተጫራቾች የጠየቁትን ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት
ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ጨረታው የሚለየው እንደአስፈላጊነቱ በጥቅል ወይም በንዕስ ዋጋ ሊሆን ይችላል፡፡
11. በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
12. ተጫራቾ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ የእቃ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና
በአቢሲኒያ ባንከ ብቻ በሲፒአ/በጥሬ ገንዘብ/በጽ/ቤቱ ህጋዊ ደረሰኝ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በጥንቃቄ
በታሸገ ፖስታ ማስያዝ አለባቸው::
13. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ዋና ኦርጅናል በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ስም
ፊርማና ሙሉ አድራሻ በመፃፍ ለእንሳሮ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀ
የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት እስከ 15ኛው ቀን እስከ 11፡30 ሰአት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
ጨረታው በ16 ቀን 4፡30 ሰአት ተዘግቶ በዚያው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት
በ5፡00 ሰአት በገልጽ ይከፈታል፡፡
14. በማንኛውም ሁኔታ ተጫራች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ወይም ተመስርቶ መጫረት አይችልም።
15. የጨረታው መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማሻሻያ
ማድረግና ከጨረታ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡አሸናፊ የሆነ ድርጅት በግዥ ፈጻሚ መስሪያቤት
አቅራቢያ በሚገኝ አቃቤ ህግ ጽ/ቤት በመቅረብ 10% ውል በመግባት ለግዥ ፈጻሚ መስሪያቤት ንብረት
ክፍል ማስረክብ አለባቸው፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፤ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ ይሆናል፣
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ብሄራዊ በአላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
- የመስሪያቤቱ መገኛ ከዞኑ ደ/ብርሃን ከተማ 86 ኪ.ሜትር ከአዲስ አበባ ደግሞ 130 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር 0912841935 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአ/ብ/ክ/ መንግስት የእ/ወ/ፍ/ቤት/የግ/ን/አስ/ቡድን/መሪ የስራ ሂደት
