የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ያገለገሉ ፈርኒቸሮችና ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Commercial Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 003/2024/25
የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ያገለገሉ ፈርኒቸሮችና ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
1. ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን ሰነድ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 211 የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከመስከረም 22 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓትድረስ ባሉት የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች ያገለገሉ ንብረቶችን ከመስከረም 22 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ትይዩ ባለው አስፓልት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኘው የቀድሞ ብራሌ ጥጥ መዳመጫ ግቢ ከጠዋቱ ከ2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በመገኘት ማየት ይችላል።
3. የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ታዛቢዎች በተገኙበት ይታሸጋል።
4. ተጫራች ለንብረቱ የሚሰጠውን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው ክፍት ቦታ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎችም አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ 2ኛፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ ያስገባል።
5. ጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሠራተኞች የመዝናኛ ክቡብ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል።
6. ተጫራች ለሚጫረትበት የንብረት ዓይነቶች የጨረታ የመነሻ ዋጋውን 25% (ሃያ አምስት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለያገለገሉ ንብረቶች አስወጋጅ (Commercial Bank of Ethiopia Disposal) በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ሲፒኦ አሸናፊ ለሚሆነው በሚገዛው ንብረት ክፍያ ላይ የሚታሰብ ሲሆን አሸናፊ ላልሆኑት ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
