በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 አስተዳደር ፋይናንስ ጽህፈት ቤት የጽህፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የተሽከርካሪዎች ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Akakai Sub City Wereda 09 Finance Bureau አቃቂ ቃሊቲ ክፍል ከተማ የወረዳ 9 አስተዳደር ፋይናንስ ጽህፈት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ፋ/ጽ/ቤት 001/2017
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 አስተዳደር ፋይናንስ ጽህፈት ቤት የሚከተሉትን ግብዓቶች ማለትም ፡-
- የጽህፈት መሳሪያዎች
- አላቂ ቋሚ የቢሮ እቃዎች
- የጽዳት እቃዎች
- የደንብ ልብስ
- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- የተሽከርካሪዎች ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል -
በዚህም መሰረት ተጫራቾች
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው::
- የቫት ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከጥቃቅንና አነስተኛ አምራች ከሆኑ አምራች የመሆናቸው ማስረጃ እና ከተቋማት የተፃፈ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጥቃቅንና አነስተኛ ጅምላ ነጋዴ ከሆኑ እንደ ማንኛውም ነጋዴ ሰነድ ገዝተው ቁጥር 6 ላይ እንደተገለፀው በባንክ የተረጋገጠ 2% ሲፒዮ ማስያዝ ይኖረባቸዋል፡፡
- በኢትዮጵያ ግብር ህጎች በተደነገገው መሰረት የግብር እና የታክስ ግዴታ
መወጣቱን የሚያመለክቱ ሰነዶች ማቀረብ የሚችል፡፡ - የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ የጨረታውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በግልጽ በመሙላትና እያንዳንዱ የገዙት ሰነድ ላይ ድርጅቱን የሚገልጽ ፊርማ እና ማህተም በመምታት ኦርጅናሉንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማድረግ ሁለቱንም ፖስታዎች በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት በፋይናንስ ፅ/ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 400.00 ብቻ በመክፈሰ ዝርዝር ጉዳዩን የያዘ ሰነድ በፋይናንስ ፅ/ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ተጫራቾች ጨይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:30 ይከፈታል አስራ አንደኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡አላቂ ቋሚ እቃዎች በፎቶ የተደገፈ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በአንድ የዕቃ መግለጫ ዝርዝር ላይ ማቅረብ የሚቻለው 1(አንድ) ናሙና ብቻ ነው፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- ለተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0941 934 362/0940 295 891 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡ አድራሻ : ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል በሚወስደው አስፋልት ላይ ቅሊንጦ ማረሚያ ዝቅ ብሎ ከከነማ ፋርማሲ አጠገብ ያለው ህንፃ ላይ 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ ጽ/ቤት
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 አስተዳደር ፋይናንስ ጽህፈት ቤት
