በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎች እና አገልግሎት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ ማሠራት ይፈልጋል
ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት
የጨረታ ማስወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ፡- ጀሞ01/2017
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በወረዳ 04 ስር የሚገኘው ጀሞ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
|
የሎት ዓይነቶች |
የዕቃው ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የብር መጠን |
|
ሎት አንድ |
የደንብ ልብስ |
7,000 |
|
ሎት ሁለት |
የፅዳት ዕቃዎች |
13,000 |
|
ሎት ሶስት |
ቋሚ እቃዎች |
17,000 |
|
ሎት አራት |
የጽህፈት አላቂ እቃዎች |
10,000 |
|
ሎት አምስት |
የቢሮ አላቂ እቃዎች |
7,000 |
|
ሎት ስድስት |
አጋዥ መጽሐፍት |
2,000 |
|
ሎት ሰባት |
የላብራቶሪ እቃዎች |
2,500 |
|
ሎት ስምንት |
ማሽነሪ ጥገና |
1,000 |
|
ሎት ዘጠኝ |
የህትመት ሥራ |
3,500 |
|
ሎት አስር |
የጥገና ሥራ |
5,000 |
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የአቅራቢዎች የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምር ዘወትር በሥራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከፋይናንስና ግዢ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 4 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት በሰንጠረዡ ስር በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ኦሪጅናል እና ኮፒ ብሎ በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11 የሥራ ቀናት 4፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከቀረበው አጭር መግለጫ (specification) ሰጪ በመሰረዝ ወይም በማሻሻል ማቅረብ እና በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት አይፈቀድም፡፡
- በጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጅተው በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በትምህርት ቤቱ ስም የተፃፈ ደብዳቤ እና የጨረታውን ቁጥር ጠቅሰው በመፃፍ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ያስይዛሉ፡፡
- ተጫራቾች ሎት 1፣ ሎት 2፣ ሎት 4፣ ሎት 5፣ ሎት 7 እና ሎት 9 የተመረጡ እቃዎችን ናሙና ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በተጨማሪም ሎት 3፣ ቋሚ እቃዎች በፎቶ በተደገፈ ማስረጃ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ሎት 9 የጥገና ሥራ ደረጃ 7 እና ደረጃ 8 የሆኑ ተቋራጮች ብቻ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በትምህርት ቤቱ ላይብረሪ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የሚከፈትበት ቀን ካላንደር የሚዘጋው ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- ከአየር ጤና ወደ ዓለም ባንክ በሚወስደው መንገድ ከወረዳ 04 ትንሽ ከፍ ብሎ፡፡
ስልክ ቁጥር፡-011-8-35-30-56
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት
