የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ በሸካ ዞን የአን/ወ/ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በወረዳ ውስጥ ያሉት ሴ/ር መ/ቤቶች ለሥራ አገልግሎት የሚውል የጽ/መሣሪያዎች፣ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ኮምፒዩተሮችና ላፕቶፖች፣ ሞተር ሳይክሎችና የሞተርና የመኪና ጎማዎች፣ ፈርኒቸር፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ የሠራተኛ ደንብ ልብሶችና የስፌት አገ/ቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ በሸካ ዞን አን/ወ/ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/በሸካ ዞን የአን/ወ/ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በወረዳ ውስጥ ያሉት ሴ/ር መ/ቤቶች ለሥራ አገልግሎት የሚውል
- የጽ/መሣሪያዎች፣ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ኮምፒዩተሮችና ላፕቶፖች፣
- ሞተር ሳይክሎችና የሞተርና የመኪና ጎማዎች፣ ፈርኒቸር፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣
- የሠራተኛ ደንብ ልብሶችና የስፌት አገ/ቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት፡-
- በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን 2017 በጀት ዓመት ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤
- ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ቲን ቁጥር ያላቸውና የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል ትችል፤
- እስከ ወረዳ ማዕከል በራሳቸው ያሸነፉትን ዕቃዎችን ማቅረብ የሚችል ትችል፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ግዥ አይነት(ሎት) 3000 /ሦስት ሺህ/ እና ለጽዳት ዕቃዎች ብር 1000 /አንድ ሺህ/ በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ የምትችሉ ሆኖ ከዚህ በላይ በተገለጸው መሠረት መስፈርቶቹን የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ 200 ብር አንድራቻ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል ዕቃዎችን የያዘ ዝርዝር ሰነድ ከአን/ወ/ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 11 በመውሰድ እያንዳንዱ ዕቃ ዋጋ በነጠላ ከነቫቱ ተሞልቶ 2 ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ በማድረግና በፖስታ በማሸግ ለጨረታ የተዘጋጀ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 11 ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
- ጨረታው በ16ተኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ 16ተኛው የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- የጨረታው ሳጥን በሚከፈትበት ወቅት ተጫራቾች (ህጋዊ) ወኪሎቻቸው ባለመገኘታቸው ጨረታውን አይስተጓጉልም፤
- ተጫራቾች ባሸነፉበት ዕቃዎች ውል ገብተው ለማቅረብ ፈቃደኛ ባይሆኑ የውል ማስከበሪያ ያስያዙት CPO ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ በጨረታ ህግና ደንብ መሠረት ለሚመለከተው አካል እርምጃ እንዲወሰድ ሪፖርት ከተደረገ በኃላ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ሊወስድ ይችላል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- በፖስታው ላይ ስም፣ ፊርማ፣ አድራሻ፣ ማህተምና ስልክ ቁጥር መኖር አለበት፣
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፣
- ያቀረቡትን ዋጋ በአሀዝና በፊደል ያለስርዝ ድልዝ መፃፍ አለበት፤ ለበለጠ መረጃ አድራሻችን ከዋናው መዲናን አዲስ አበባ እስከ ጌጫ 711 ኪ/ሜ፣ ጅማ እስከ ጌጫ 380 ኪ/ሜ፣ ከሚዛን እስከ ጌጫ 100 ኪ/ሜ፣ ከቴፒ እስከ ጌጫ 52 ኪ/ሜ ፣ ከማሻ እስከ ጌጫ 37 ኪ/ሜ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ በሸካ ዞን አን/ወ/ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
