በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ ደረጃውን የጠበቀ የተለያዩ ዓይነት ያላቸው ፖሊ ባግ (Poly Bags) በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ - ኢምዘደውአዘ/ጨሽ/01 ሠነድ/2017
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ ደረጃውን የጠበቀ የተለያዩ ዓይነት ያላቸው ፖሊ ባግ (Poly Bags) በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
1. ማንኛውም ተጫራች የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡
2. ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ከ2% ያላነሰ CPO በኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ ስም ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታው ዋጋ ለ30 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል፡፡
3. የጨረታ ሰነዱ ዘወትር በስራ ሰዓት (ከ11፡00 ሰዓት በፊት) በዘርፉ ፅ/ቤት ቤት ቃሊቲ ጉምሩክ ፊት ለፊት የኢትዯጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4 የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ ።
4. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፤
5. ጨረታው መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፉ ቢሮ ቁጥር 4 ይከፈታል፡፡
6. ዘርፉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 011 6 18 61 25
የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ
