የወራቤ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2017 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች እና መድሃኒቶችን በጨረታ መግዛት ይፈልጋል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የወራቤ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2017 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ
- ሎት1 የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች እና
- ሎት2 መድሃኒቶችን በጨረታ መግዛት ይፈልጋል በመሆኑም ተጫራቾች ስለዕቃዎች ዝርዝር የሚገልፅ ሰነድ (ዶክመንት) በወራቤ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 302 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ለእያንዳንዳቸው በመክፈል ዘወትር በስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡
1. ተጫራቾች ተፈላጊ ዕቃዎችን ማቅረብ የሚያስችላቸውን በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የኢትዮጵያ የምግብ እና የመድሃኒት ባለስልጣን የታደሰ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. የዚህ ጨረታ ተካፋዮች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፣ የምስክር ወረቀት ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ 15000 በባንክ በተመሰከረ CPO /ሲፒኦ/ የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (በአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30-6፡30 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡30-11፡30 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ክፍል ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
5. ጨረታው በ15 ኛው ቀን በ08፡00 ተዘግቶ በዕለቱ ከሰዓት በኋላ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ የመክፈቻውም ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በህዝባዊ በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
6. ሆስፒታሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 3299 270 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የወራቤ ኮምሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
