በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሠልጠኛ ት/ቤት የፅህፈት ዕቃዎች የፅዳት ዕቃዎች፣ የኤሌትሪክና የቧንቧ ዕቃዎች፣ የተለያዩ የህሙማን ቀለቦች፤ የተለያዩ የስፖርት ማሊያዎች፤ አንሶላዎች የስፖርት ሸራ ጫማዎች ፤ የተለያዩ የህሙማን ቢጃማዎች የእጅ ጓንቶች ወዘተ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ።
Education and Training Department of the Federal Ministry of National Defense
የብሔራዊ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሠልጠኛ ት/ቤት የፅህፈት ዕቃዎች የፅዳት ዕቃዎች፣ የኤሌትሪክና የቧንቧ ዕቃዎች፣ የተለያዩ የህሙማን ቀለቦች፤ የተለያዩ የስፖርት ማሊያዎች፤ አንሶላዎች የስፖርት ሸራ ጫማዎች ፤ የተለያዩ የህሙማን ቢጃማዎች የእጅ ጓንቶች ወዘተ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ።
በመሆኑም:-
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ እና ከግዥ ኤጀንሲ የተሰጠ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ ሲያቀርቡ የእቃው ሙሉ ስም የተሰራበትን ሀገር እና የጥራት ደረጃዉን/specification/ አሟልተው ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ስነ-ስርዓት እና ይህንኑ አስመልከቶ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግስት ባወጣው የግዥ አዋጅ ቁጥር 649/2001 መመሪያ/2002 መሰረት ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው።
- የጨረታ ሰነዶች ማስገቢያ የሚሆነው ጦላይ የከፍ/ባለሌላ ማዕረግተኛ ማ/ት/ቤት ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ቢሮ ቁጥር 28 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከመስከረም 14/01/2017 ዓ.ም እስከ መስከረም 28/01/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተ/ቁ 4 በተገለጸው አድራሻ ሆኖ በቢሮ ቁጥር 28 መስከረም 28/1/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ ብር ብቻ በመከፈል በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጦላይ ከፍ/ባለሌላ ማዕረግተኛ ማ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 28 ግዥ ዴስከ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በተጨማሪ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የከፍ/ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ት/ቤት
/MINSTRY OF NATIONAL DEFENCE SINOR NON COMMISION OFFICER
TRANNING SCHOOL በሚል በማንኛውም ሀጋዊ ባንክ የ50.ዐዐዐ /ሃምሳ ሺህ ብር/ ሲፒኦ ከጨረታ
ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- አሸናፊው ድርጅት በጨረታ ሠነድ ላይ የተጠቀሱትን ዕቃዎች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ውል ካሰረ በ20 ቀናት ውስጥ እቃውን አጠናቆ ጦላይ ማሰልጠኛ ት/ቤት ማስገባት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ሰነዱን በሚገዙበት ወቅት ማሰልጠኛ ት/ቤቱ ያቀረባቸውን የእቃ ሳምፕሎች በማየት ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል። ሌላ ማሰልጠኛ ት/ቤቱ ያላቀረባቸው የእቃ ሳምፕሎች ካሉ አሸናፊ ድርጅቶች ሳምፕሎችን ውል በሚያስሩበት ወቅት ለመስሪያ ቤቱ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መስሪያ ቤታችን የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች በንግድ ስያሜያቸው ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ አካውንት ቁጥር ሊኖራቸው ይገባቸዋል።
- በጨረታ አሸናፊ የሚሆኑት ድርጅቶች የውል ማስከበሪያ ዋስትና ሲያስይዙ ካሸነፉት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10%/አስር ፐርሰንት/ የባንከ ጋራንት ወይም CPO ማስያዝ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያው ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ ማድረግ አለበት።
- ተጫራቾች አሸናፊ የሚሆኑት ለእያንዳንዱ እቃ በሚያቀርቡት እቃ አነስተኛ ዋጋና ጥራት ያለው እቃ ይሆናል።
- ተጫራቾች ሰነዳቸውን ሲያቀርቡ ኦርጅናልና ኮፒ ብለው መለየት አለባቸው፤
አድራሻ፡- ክልል ኦሮሚያ ዞን ጅማ ቦተር ጦላይ ወረዳ ላይ ይገኛል ለተጨማሪ ማብራሪያ በቢሮ
ስልክ ቁጥር፡- 0113880012
በሞባይል ስልክ ቁጥር 0937991475/0947981639/0910449613 ይደውሉ
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የከፍተኛ ባለሌላ ማዕ/ማሰ//ት/ቤት ጦላይ
