በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የገንደቆሬ ጤና ጣቢያ እና የደቻቱ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዢዎችን ለመፈፀም አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የገንደቆሬ ጤና ጣቢያ እና የደቻቱ ጤና ጣቢያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ገ/ቆ/ጤ/ጣ -
በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የገንደቆሬ ጤና ጣቢያ እና የደቻቱ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዢዎችን ለመፈፀም አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡ በዚሁ መሠረት በጨረታው ላይ
ሎት 1 - የቢሮ የጽህፈት መሣሪያዎች፣
ሎት 2 - የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች፣
ሎት 3 - ህትመት!
ሎት 4 - የተለያዩ መድሃኒቶች እና የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች፣
1.1 ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ
ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
1.2. በመንግስት ግዢ አቅራቢ የተመዘገቡና የተመዘገቡበትን ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
13. ተጫራቾች የታከስ መለያ ቁጥር (TIN No) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
1.4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ለ15 ተከታታይ
የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በገንደቆሬ ጤና ጣቢያ
በግ/ፋ/ንብ/አስ/ድ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
1.5. መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለእያንዳንዱ ሎት ብር 10,000.00
/አስር ሺህ ብር/ ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም /CPO/ ወይም (BID
BOND) ከጨረታው ኦሪጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
1.6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ
መቀበያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
1.7. የጨረታ ሰነዱ የሚከፈትበት ቀን ይህ ጨረታ በድሬ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት
ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን ጠዋት 2፡30 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው
በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
1.8. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ እንደተገለፀለት አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ
ከጤና ጣቢያው ጋር ውል መፈራረም አለበት፡፡ ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ
ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
1.9. ተጫራቾች ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን እና ፊርማቸውን እንዲሁም የተሟላ
ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው ::
ማሳሰቢያ፡- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- 0251-13-07-61 መደወል ይቻላል፡፡ ሞባይል፡- 09-24-12-45-10
በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የገንደቆሬ ጤና ጣቢያ
