Tender Detail

Tender Details

  • Company የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን
  • Address ግሎባል በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ግቢዎች ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-42-52-36-99
  • Website
  • Deadline10 Oct 2024, 5:09 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Spare Parts

የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ከገንዘብ ሚኒስቴር የመንግስት የልማት ድርጅቶች ባለአደራ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል የተላለፉለት በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግቢ የሚገኙ በመለዋወጫ መልክ የሚሸጡ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን


የጨረታ ማስታወቂያ

በመለዋወጫ መልክ የሚሸጡ ተሸከርካሪዎች

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር LAMC/BD/02-01/2017

 

የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ከገንዘብ ሚኒስቴር የመንግስት የልማት ድርጅቶች ባለአደራ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል የተላለፉለት በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግቢ የሚገኙ በመለዋወጫ መልክ የሚሸጡ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመስከቱትን መመዘኛዎች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መመዘኛዎች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ግሎባል በሚገኘው ከንግድ ስራዎች ኮርፓሬሽን ጀርባ ባለው የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት ፋይናንስ ከፍል በመምጣት የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ንብረቶቹ የሚገኙበት አድራሻ ሳሪስ አቦ አካባቢ በሚገኘው በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ ነው፡፡
  3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በመለዋወጫ መልክ የሚሸጡ ተሽከርካሪዎች በተራ ቁጥር 2 ላይ በተጠቀሰው ቦታ /አድራሻ/ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት ፋይናንስ ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ በ 5፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመከፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  6. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይደረጋል፡፡
  7. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለፁትን አሟልቶ መገኘት ነው ።
  8. አሸናፊ ተጫራቶች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ1ዐ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
  9. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር፡- 09-42-52-36-99/09-12-13-47-91 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
  10. ኮርፖሬሽኑ በማናቸውም ጊዜ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን

Save Tender