የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ከተሞች ውስጥ ለስኳር ማከማቻ የሚያገለግሉ መጋዘኖች በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ውል በመዋዋል ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር LP/OT/09/SIG/2017
1. የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ከተሞች ውስጥ ለስኳር ማከማቻ የሚያገለግሉ መጋዘኖች በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ውል በመዋዋል ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
• ሎት-1 አዲስ አበባ ከተማ 100,000 ኩንታል የመያዝ አቅም ያለው መጋዘን፤
•ሎት-2 አርባ ምንጭ ከተማ 50,000 ኩንታል የመያዝ አቅም ያለው መጋዘን፣
• ሎት-3 ሻሽመኔ ከተማ 50,000 ኩንታል የመያዝ አቅም ያለው መጋዘን፤
• ሎት-4 ነቀምት ከተማ 50,000 ኩንታል የመያዝ አቅም ያለው መጋዘን፤
2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ ለ2016/17 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታከስ ክሊራንስ/ በጨረታ መሳተፍ እንዲችል የድጋፍ ምስከር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No.) ሠርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስከር ወረቀት እና የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ የሚመለከተው የመንግስት አካል ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች አገልግሎት ሰጪ ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን/ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::
3. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በመክፈል ወይም በኢትየጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር1000000888862 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ፣ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00 ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ መስከረም 24 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት-1 ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ለሎት-2፤ ለሎት-3 እና ለሎት-4 ለእንዳንዳቸው ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተመሠከረለት ቼክ (CPO) ብቻ ከቴክኒክ መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለዘጠና (90) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
7. የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለስልሳ (60) ቀናት ይሆናል፡፡
8. ግሩፑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ
ሚከሲኮ አካባቢ ከሚገኘው አልሳም ጨለለቅ ህንፃ ፊት ለፊት፣
ፈሲፒስ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220
ስልክ ቁጥር +251 11 5 50 04 17 011551 62 71
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
