የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ከመንግስት በተመደበ በጀት በሎት 1፡- የማዕቀፍ ሕትመት ስራዎች በሎት 2፡- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ።
Dredawa Administration Government Communications Office (የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨ/መ/ቁመኮ01/2017
የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ከመንግስት በተመደበ በጀት በሎት 1፡- የማዕቀፍ ሕትመት ስራዎች በሎት 2፡- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ።
በመሆኑም፡-
- ተጫራቾች በህትመት ስራ እና በኤሌክትሮኒክስ የተሰማሩና በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድና በመንግስት የእቃና አገልግሎት አቅርቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋየዕ መለያ ቁጥር ያላቸው ፤
- ተጫራቾች ከላይ የተገለፁትን የህትመት አይነቶች ሳምፕል የሚጠይቁ በሆኑት ከዚህ በፊት በድርጅታቸው የሰሯቸውን ለሳምፕል ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ጨረታ አግባብነት ያለው የተሟላ ማስረጃና ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ጨረታው እስከ የሚታሸግበት እለትና ሰዓት ቀደም ብሎ የጨረታ ሰነዱን ከቢሮው የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 112 ቀርበው የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ተጫራቾች አስፈላጊውን የቴክኒካል እና የፋይናንስ ሰነድ ለብቻ ለብቻ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ገልፀው ማስገባት ይኖርባቸዋል ።
- የጨረታ ሳጥኑ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት በስራ ሂደቱ ቢሮ በግልፅ ይከፈታል ።
- ተጫራቾች ለሎት 1፡- ብር 15,000 ለሎት 2፡- ብር 20,000 ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ፣ በጥሬ ገንዘብ ፣ በባንክ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት እንዲሁም ከነዚህ አማራጮች በአንዱ በመጠቀም ለብቻው በአንድ ፓስታ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ቢያስፈልግ በሚከተለው አድራሻ መጠቀም ይችላሉ ፡-
የስልክ ቁጥር 0252-11-60-62
የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ድሬዳዋ
