በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ።
A.A City Administration Code Enforcement Authority (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፦ አ/አ/ደ/ማ/ባ/እቃ/ግ/ጨ/01/2017
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ።
|
ሎት ቁጥር |
የሚገዛው የእቃ ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) መጠን |
ምርመራ |
|
1 |
የህትመት ውጤቶች |
8,000.00 |
|
|
2 |
የሆቴል አገልግሎት /ለአ/አ ባለ 5 ኮከብ ፣ ለአዳማ እና ለደብረዘይት ባለ 4 ኮከብ |
20,000.00 |
|
|
3 |
የታሸገ ውሃ ግማሽ ሊትር (1/2) |
5,000.00 |
|
|
4 |
የመኪና እቃዎች |
8,000.00 |
|
|
5 |
የደንብ ልብስ |
200,000.00 |
|
|
6 |
አላቂ የፅዳት እቃዎች |
7,000.00 |
|
|
7 |
ቋሚ እቃዎች |
5,000.00 |
|
|
8 |
ክርስቲያል ዋንጫ /ለሽልማት አገልግሎት የሚውል |
10,000.00 |
|
|
9 |
የኤሌክትሮኒክስ ጥገና |
10,000.00 |
|
|
10 |
የፕሪንተርና ፎቶ ኮፒ ቀለም |
11,000.00 |
|
|
11 |
የአየር ሰዓት አገልግሎትና የጋዜጣ አምድ |
6,000.00 |
|
|
12 |
ለቢሮ አገልግሎት የሚያስፈልጉ ቋሚ እቃዎች |
10,000.00 |
|
|
13 |
ለቢሮ ማስዋቢያ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች (አርቴፊሻል እና የተፈጥሮ አበባዎች ከነማስቀመጫው) |
5,000.00 |
|
|
14 |
የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች |
60,000.00 |
|
|
15 |
ለቢሮ መስተንግዶ የሚውሉ |
4,000.00 |
|
በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ ፡-
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ።
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ።
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን /TIN / ማቅረብ የሚችሉ ።
- የአቅራቢነት ምዝገባ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ዘወትር ከሰኞ እስከ እሁድ ከ2፡30 11፡00 ሰዓት ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 08/15 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለየብቻው በማቅረብ በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ግዥና ንብረት አ/ጠ/አ/ዳይሬክቶሬት 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09/15 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል ። የሚቀርበው ዋጋ ማቅረቢያ ፊርማና ማህተም ከሌለው ተቀባይነት አይኖረውም ። ናሙና የተጠየቀባቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው ።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት ይከፈታል ።
- ተጫራቾች በሚጫረቱበት እያንዳንዱ እቃ ጥራት በቴክኒክ ብቃታቸው ከተመረጡ በዋጋ የሚወዳደሩ ይሆናል ።
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡት የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም ።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
አድራሻ ፡- አዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ (ፒያሳ) ልዩ ስሙ እሪ በከንቱ ተብሎ በሚጠራው የኢትዯጵያ
ስታቲስቲካል አገልግሎት ቢሮ አካባቢ እስጢፋኖስ መካሻ አማረ (EMA) ህንፃ 9ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 011-5-62-23-43 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
