የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ ተይዞ የተወረሰ 40,200 ሊትር Heavey Fuel Oil በሃራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
የአዳማ
የሃረጅ ጨረታ ማስታወቂያ
ሃራጅ ቁጥር 01/2016
የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ ተይዞ የተወረሰ 40,200 ሊትር heavey Fuel Oil በሃራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶችን የምታሟሉግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፡-
1. በአዳማ ጉ/ቅ/ቤት ለጨረታ በቀረበው Heavey Fuel Oil ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራችበጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችንያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን ከመጨረቻ ሰነዱ ጋርተያይዞ ለሃራጅ ጨረታ ጨረታው በሚካሄድበት ቀን ማቅረብ ይኖርበታል።
2. የሃራጅ ጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዘወትርከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት በአካል በአዳማ ከተማ በከልቻትራንስፖርት ኢማ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የቅ/ ጽ/ቤቱ የገቢ ሂሳብና ዋስትናዎች አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር11 የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመግዛት በጨረታ የወጡትን ዕቃዎችን ማየት የሚትችሉ መሆኑንእንገልፃለን፡፡
3. በሃራጅ ጨረታ ለምትወዳደሩ ለጨረታው ዋስትና የሚሆን ማለትም ለምድብ Heavy Fuel Oil 275,287.58(ሁለት መቶ ሰባ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ሰማንያ ሰባት ብር ከሀምሳ ስምንት ሳንቲም) በባንክተመሰከረለት (CPO) Customs Commission Adama Branch Office ስም በማሰራት በተራ ቁጥር 1 ላይከተጠቀሱት ሰነዶች ጋር በማያያዝ ለሃራጅ ጨረታ ጨረታው በሚካሄድበት እለት ይዛችሁ መቅረብይኖርባችኋል፡፡
4. በጨረታ ሽያጭ የእቃው አስመጪ ወይም ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም፡፡
5. በሀራጅ ጨረታ ለሽያጭ ለቀረበው heavy fuel oil የቅ/ጽ/ቤቱ የውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮበአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ አዲስ በተከራየው ቢሮ ግቢ በመገኘት ጨረታውን ለመሳተፍየሚያስፈልገውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት CPO፣ የጨረታ ሰነዱን እና በተራ ቁጥር 1 ላይከተጠቀሱት ሌሎች ሰነዶች ጋር ሃራጅ ጨረታ በሚካሄድበት ቀን እና ሰዓት ይዛችሁ መገኘት አለባችሁ፡፡
6. በሀራጅ ጨረታ ለመሸጥ የውጣው Heavy Fuel Oil እቃ በአዳማ ከተማ በከልቻ ትራንስፖርት አ.ማ ቅጥርግቢ ውስጥ በሚገኘው መጋዘን ቁጥር 10 በነዳጅ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ቦቴ ላይ ተጭኖ ስለሚገኝ የሃራጅጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላበስድስተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን፤ ስድስተኛው ቀን በዓል ወይም እሁድ ቀን ከሆነበሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚካሄድ ይሆናል።
7. የሀራጅ ጨረታው የሚካሄደው የቅ/ጽ/ቤቱ የውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ በአዳማ ከተማ በሬቻአካባቢ መ/ቤቱ አዲስ በተከራየውቢሮ ግቢ ውስጥ ሲሆን ጨረታው ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውባሉበት ይካሄዳል።
8. የሀራጅ ጨረታ ዕቃው የመነሻ ዋጋ ያልተወሰነለት ስለሆነ የመነሻ ዋጋው በተጫራች የሚሰጥ ይሆናል፡፡
9. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3/ሶስት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
10. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ይሸነፉበትገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
11.ከላይ በተ/ቁ 10 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንበረቱን ያልወሰደ ተጫራቾችለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል።
12. ለጨረታ የቀረቡው እቃ ሽያጩ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይምተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም፡፡
13. ማንኛውም ተጫራች 100 ብር ሰነድ የገዛበትን ደረሰኝ ከሌሎች ሰነዶች ጋር አያይዞ ለሃራጅ ጨረታጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዞ መገኘት አለበት፡፡
14.ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
15. ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክየማንቀበል መሆኑን አናሳስባለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች፡- 022-111-84-29 እና 022-211-89-25 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት
