የሰሊጥና የእህል ማበጠሪያ ማሽን የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት አቢሲኒያ ባንክ እና የፍ/ባለዕዳ ናይል ቡና ላኪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር መካከል ስላለው የፍርድአፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/69405 በ28/1/03 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ/99259 በህዳር29 ቀን 2003 ዓ/ም በሰኔ 9 ቀን 2003 ዓ.ም በ18/5/2003 ዓ.ም በ3/10/2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠውትዕዛዝ መሠረት በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 7 በፍ/ባለዕዳ መጋዝን የሚገኝ የሰሊጥና የእህል ማበጠሪያማሽን የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 10,614,551.64(አስር ሚሊዮን ስድስት መቶ አስራ አራት ሺህ አምስት መቶ ሃምሳአንድ ብር 64/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 14 ቀን 2017 ዓ.ምበሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ ሰዓት 8፡30 ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበውእንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀምዳይሬክቶሬትሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርትንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅትየንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ 1/4ኛውአስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብአሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ዳ/ ስም CPO አሰርቶበኢትጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ የፍ/አፈ ዳይሮክቶሬትንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወርግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት
