የመኖሪያ ቤት እና የመኪና የሐራጅ ሽያጭ
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ወ/ሮ ደመቀች ወንድማገኝ እና በፍ/ባለዕዳ አቶ ሙሉጌታ አባተ መካከል ስላለው የፍርድአፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 130648 በ4/6/2016 ዓ.ም እና በመ/ቁ 02115 በ27/6/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቤ.ቁ 1610 የሆነውየቦታ ስፋት 108 ካ.ሜ ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤት ፍርድ ያረፈበት ቤት ቁጥር ቦሌ13/2/225/137-6468/41133/01 የተመዘገበ ካርታ ያለው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 5,788,308 (አምስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰማኒያስምንት ሺህ ሶስት መቶ ስምንት ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 15 ቀን 2017 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾችተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል። 2ኛ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 6 ሮሆቦትየመኪና ማቆሚያ ግቢ ውስጥ የሚገኝ የሠ/ቁ/ኮድ 2-A14026 አ.አ የሆነው መኪና የሆነው የሐራጅ ሽያጭመነሻ ዋጋ ብር 900,000 (ዘጠኝ መቶ ሺህ ብር) ሆኖ የስም ማዘወርያ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም15 ቀን 2017 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾችተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀምዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርትንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን ፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅትየንብረቱን ግምት ¼ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦምሆነ አሳንሶ C.P.O የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊየሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ዳ/ስም C.P.O አሰርተው በኢትዮጵያንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት የፍ/አ/ዳይሬክቶሬትንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወርግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት
