Tender Detail

Tender Details

  • Deadline21 Aug 2024, 9:29 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Organizational

የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


የሐራጅ‍‍‍‍‍‌‌‌‍‍‌‌‌‍‌ ሽያጭ ማስታወቂያ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎

በፍ/ባለመብት እነ አቶ ይስሀቅ አበጋዝ እና በፍ/ባለዕዳ አቶ ጌራወርቅ አክሊሉ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 198981 በ13/0/2016 ዓ.ም እና መ/ቁ 200913 በ16/11/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 12 የቤ.ቁ ቢ13/9 የሆነው በካርታ ቁጥር AA00008105896130219 የተመዘገበ የቦታው ስፋት 60.52 ካ.ሜ በሟች ወ/ሮ ሕይወት አበጋዝ ተመዝግቦ የሚገኝ ቤት የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 2,302,301.84 (ሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሁለት ሺህ ሶስት መቶ አንድ ብር ከ84/100 ሳንቲም) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆመስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡30 ሰዓት‍‍‍‍‍‌‌‌‍‍‌‌‌‍‌ ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው አይካፈልም፡፡

በጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታ‏‏‏‏‏‎‎‎‏‏‎‎‎‏‎ውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ዳ/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት የፍ/አ/ዳይሬክቶሬቱ ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች
የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት

 

Save Tender