የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አስተዳደር
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 001/2017
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 የበጀት ዓመት የተለያዩ ሎቶች ላይ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ፡-
- ሎት 1፡- የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት 2፡- የደንብ ልብስ
- ሎት 3፡- የሕትመት ሥራዎች
- ሎት 4፡- የመድረክ ዝግጅት
- ሎት 5 - የመኪና ኪራይ
- ሎት 6፡- የጉልበት ሥራ
- ሎት 7፡- የከባድ መኪና ጥገና
- ሎት 8፡- የከባድ መኪና ጎማ ጥገና (ጎሚስታ)
- ሎት 9 –የከባድ መኪና እጥበት
በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት አሟልተው በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡
- የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና ክሪላንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከወጣው ጨረታ ውስጥ ብር 100,000.00 / አንድ መቶ ሺህ ብር/ በላይ ዋጋ በማቅረብ በጨረታው የሚሳተፍ ማንኛውም የአገር ውስጥ ተጫራች የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ወረቀት ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል ፡፡
- ጨረታ ሰነዱን በሥራ ሰዓት ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በሥራ አስኪያጅ ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 504 ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአንድ ኤንቨሎፕ የሚቀርብ ሆኖ ኦርጅናል ዶክመንት እና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለየብቻ ሆኖ በአንድ ፖስታ በማጠቃለል ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሎት 1 ፣ 2 ፣ 3 ፡ 4 ፡ 5 ፡ 6 ፡ 8 እና ሎት 9 የሆኑትን ብር 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ሆኖ ሎት 7 ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ በኮ/ቀ/ከ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት በሚል በማዘጋጀት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት የተደራጁ ከሆነ ከተደራጁበት ተቋም የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው ቀን ጠዋት 3፡30 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ነገር ግን ከኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
- ተጫራቾች በሎት 1፡-የደንብ ልብስ፣ ሎት 2፡-የጽዳት ዕቃ እና ሎት 3፣የህትመት ስራዎች ላይ የሚጫረቱ የዕቃ ናሙና/sample/ የጨረታ ጊዜው ሳያልቅ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ጨረታ ሰነድ ስርዝ ድልዝ ኖሮት ካልተፈረመ፣ ፍሉድ ተጠቅሞ በጉልህ የማይነበብ ከሆነ ከውድድር ወጪ ይሆናሉ፡፡
- መ/ቤቱ ከአሸናፊው ተጫራች ውል ከመፈረሙ በፊት በአሸናፊ ተጫራች አቅርቦት መጠን ላይ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20% መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል ይሆናል፡፡
- የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆኑ፤ ለወደፊትም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ እና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንደሚወረስ ማወቅ አለባቸው፡፡
አድራሻችን፡- ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ህንጻ 5ኛ ፎቅ ቢ/ቁ 504
በሥራ አስኪያጅ ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን
ለበለጠ መረጃ፡- 011-835 -88 – 99 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት
