የአለልቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2017 የበጀት ዓመት የተለያዩ ቋሚና አላቂ እቃዎች፣የጽዳት እቃዎች፣የኤሌትሮኒክስ ዕቃዎች የመኪና እና የሞተር ጎማዎች፣የደንብ ልብስ እና ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና የተለያዩ ደረሰኞችን ለማሳተም ይፈልጋል
የአለልቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር በሰሜን ሸዋ ዞን የአለልቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2017 የበጀት ዓመት የተለያዩ ቋሚና አላቂ እቃዎች፤ የጽዳት እቃዎች፤ የኤሌትሮኒክስ ዕቃዎች የመኪና እና የሞተር ጎማዎች፤ የደንብ ልብስ እና ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና የተለያዩ ደረሰኞችን ለማሳተም ይፈልጋል። ስለዚህ የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ የጨረታ መመሪያው ከሰነዱ ጋር የተያያዘ መሆኑን እናሳውቃለን።
ጨረታው የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት 15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀን ቆይቶ በ22/12/2016 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት ከቀኑ 8፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
አድራሻ፡- በደሴ መንገድ በዋናው አስፋልት ከአ/አ 55 ኪ.ሜ በስተቀኝ 150 ሜትር ገባ ብሎ ነው።
በስልክ ቁጥር 0920 219 543 የአለልቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መጠየቅ ይችላሱ።
የአለልቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
