ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የማልካ ኖኖ ክፍስ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት
የማለካ ኖኖ ከፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ፍ/ቤቱ የሚጠቀመው አላቂ ዕቃ፡ የደንብ ልብስ፣ፈርኒቸር፣ኤሌከትሮኒከስ፣ እስቴሽነሪዎች፣ እና የፅዳት ዕቃዎች ለፍ/ቤቱ የሚያገለግል አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህበጨረታው መወዳደር ነጋዴዎች እና ባለሁበቶች ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎችበሙሉ መወዳደር የምትችሉ ይሆናል፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የታደሰ እንዲሁም የሚፈለግባቸውን ግብር አጠናቀውስለመከፈላቸው በቂ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
2. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናትከማለካ ኖኖ ከፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል መግዛትይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000( ሃያ ሺ ብር) በባንክ በተመሰከረለት CPO የማለካ ኖኖ ከፍለ ከተማ ወረዳፍ/ቤት ስም አዘጋጅቶ ከማጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ የሚሸጡበትን ዋጋ በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በተባለው ቀንውስጥ ለጨረታ ለተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች የተሟላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም፡፡
6. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፤ እንዲሁም ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋቫትን (15%) ያካተተ መሆን አለበት፡፡
7. ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃዎች መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ ድርስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃዎች ፍ/ቤቱ ካዘዘ በኋላ የታዘዘው ዕቃ አሸናፊው ለናሙና ለፍ/ቤቱ ማቅረብ የሚችል እናገቢ የሚሆነው አስፈላጊውን ጥራት ማሟላቱን በባለሙያ ሲረጋገጥ ይሆናል፡፡
9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ ከእስቶካቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
10. የጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰውቀን በ8፡ዐዐ የሚከፈት ይሆናል፡፡
11. ከላይ የተገለፀው የመከፈቻ ቀን በዓል ወይንም የሰንበት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በቀጣዩ የስራ ቀንይሆናል፡፡
12. ፍ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም ምርጫ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 2601258
የማልካ ኖኖ ክፍስ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት
