በገቢዎች ሚኒስቴር ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ተሽከርካሪ መኪና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ግልጽ የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 3/2016
በገቢዎች ሚኒስቴር ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 ንዑስ አንቀፅ 9 መሰረት የሚፈለግባቸውን የታከስ ዕዳ በህግ በተቀመጠው ጊዜ ባለመከፈላቸው ምክንያት ንብረቱ የጁዲ አግሪካልቸራል ዴቨሎፕመንት ኃላ/የተ/የግ ማህበር ንብረት የነበረው ተሽከርካሪ መኪና የሠሌዳ ቁጥር 03-04909 ድሬ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
1. የሐብቱ የጨረታ መነሻ ዋጋ ግምት ብር 1,593,776.75
2. በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች በማንኛውም ዘርፍ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 310 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
4. በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው መኪና የጨረታው መነሻ ዋጋ 1/10ኛውን ብቻለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በድሬዳዋ ቅ/ፅ/ቤት የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ በገቢዎች ሚኒስቴር ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ስም በባንክ አሰርቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይኖርባቸዋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የመስሪያ ቤቱ ስም |
ለጨረታ የቀረበው የንብረት ዓይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ |
የጨረታ የመዝጊያና የመከፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
የገቢዎች ሚኒስቴር የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት |
ተሽከርካሪ መኪና |
እስከ መስከረም 07/2017ዓ.ም |
መስከረም 08/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡45 ሰዓት ተዘግቶበዚያው እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ |
6. የጨረታው የመክፈቻ ቦታ፡- በገቢዎች ሚኒስቴር ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት በዕለቱ በሚዘጋጀው ቦታ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
7. የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ዋስትና ያስያዙ (CPO) የሚከፍሉት ዋጋ እንደ አስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
8. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለፃላቸው ቀን ጀምሮ ባሉበት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ መ/ቤቱ በሚሰጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ያሸነፉትን ንብረት/ ሃብት መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
9. ከላይ በተራ ቁጥር 7 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ በድጋሚ እንዳልተሸጠ ተቆጥሮ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
10. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 025-4-11-74-59/ 025-1-11-07-73 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት
