ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
1. የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ ለ2017 በጀት ዓመት ለዋና ጽ/ቤትና ለገቢ ማመንጫማዕከላት ለሥራ አገልግሎት ላይ የሚውሉ፡-
- ሎት 1፡- ለሆቴል አገልግሎት የሚሆኑ የምግብ ግብዓቶች፣
- ሎት 2፡- ለሆቴል መኝታ አገልግሎት የሚሆኑ አልባሳት፣
- ሎት 3፡- ለእንጨትና ብረታ ብረት ወርክ ሾፕ ለሥራ አገልግሎት የሚሆኑ የፋብሪካ ውጤቶች፣
- ሎት 4፡- ለቢሮ ሥራ አገልግሎት የሚሆን የጽህፈት መሳሪያዎች፣
- ሎት 5፡- ለቢሮ ሥራ አገልግሎት የሚሆኑ ሞተር ሳይክሎችን፣
- ሎት 6፡- ለእርሻ ሥራ አገልግሎት የሚሆን ትራክተር እና የትራክተር ተቀፅላ፣
- ሎት 7፡- የወተት ማሸጊያ ማሽን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤
ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ማሟላት አለበት።
- የታደሰ ንግድ ፈቃድና የንግድ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪእሴት ታክስ vAT/ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የታክስ መለያ ቁጥር (TIN No.) ያላቸው።
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚኖሩት 15 የሥራ ቀናትውስጥ የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከታችየተቀመጠውን አድራሻ በመጠቀም ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሎት 1 እና 3 የጨረታ ማስከበሪያ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፣ ለሎት 6 እና 7 የጨረታማስከበሪያ ብር 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) እና ለሎት 2፣ 4 እና 5 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሃምሳሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ሎት 1፣ 2፣ 4 እና 5 ይህ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት አስራ አምስተኛ (15ኛ) ቀን እስከ አስራአንደኛ (11፡00) ሰዓት ታሽጎ አስራ ስድስተኛ ቀን በጠዋቱ 3፡30 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ቀኑ በህዝብበዓላትና የእረፍት ቀን ላይ ከዋለ ቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- ሎት 3 ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት አስራ አምስተኛ ቀን እስከ አስራ አንደኛ (11፡00) ሰዓት ታሽጎ በአስራ ስድስተኛ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ቀኑ በህዝብ በዓላትና የእረፍት ቀንከዋለ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
2. የጨረታ ውድድር ሂደት እንደተጠናቀቀ ውጤቱ በኢንተርፕራይዙ በኩል ለተወዳዳሪዎች ባስመዘገቡትአድራሻ አማካይነት ይገለጽላቸዋል፤
3. ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ፡- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ፖሊሲና ልማት ሕንፃ ወይም ተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬትበሚገኝበት ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046 21 228 58 /09 24 38 81 28 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ
