የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የአረም ማጥፊያ ኬሚካል (Herbicide for Narrow & bread leaved Weed Control, Gesapax combi 500EC) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር MSF/LP/09/2024
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፀውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ጥቅል አንድ፣ የአረም ማጥፊያ ኬሚካል (Herbicide for Narrow & bread leaved Weed Control, Gesapax combi 500EC)
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
1. ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች ለእያንዳንዱ ጥቅል የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሠዓት ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ሕንፃ ግዥ ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 215 የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሲገዙ የንግድ ፈቃድ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሠነድ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ አቅራቢዎች የምዝገባ ሠርተፍኬት እና ለጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ከ1.5 - 2% የሚሆን በሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ (Proforma invoice) ላይ በማዘጋጀት በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እ.ኢ.አ ነሐሴ 14 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ድረስ ሜክሲኮ ፊሊፕስ ሕንፃ ቢሮ ቁጥር 119 ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ጨረታው በዕለቱ ነሐሴ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 119 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
7. ፋብሪካው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 0115-505607,0115-505633
ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ሕንፃ
አዲስ አበባ
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ
