የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት እነ አቶ አለሙ በቀለ እና በፍ/ባለዕዳ ህፃን አስታው አበበ በቀለ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 214103 በ2/7/2014 ዓ.ም እና በመ/ቁ 284594 በ27/7/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በልደታ ክ/ከማ ወረዳ 04 የቤ.ቁ 282/283 እና በዚህ ቤት ውስጥ የሚገኙ 15 ክፍል ቤቶች የካ/ቁ ል-08/775/8392/00 የተመዘገበ ካርታ ያለው የግቢው ስፋቱ በካርታና በአየር ካርታ መሠረት 571 ካ.ሜ በካርታና በአየር ካርታ መሠረት ቤቱ ያረፈበት ስፋት 185 ካ.ሜ በካርታና በአየር ካርታ መሠረት በፕሮፖርሽን ከግቢው ለቤቱ የሚደርሰው የቦታ ስፋት 241 ካ/ሜ በካርታና በአየር ካርታ መሠረት ለግለሰቡ የሚደርሰው የቦታ ስፋት 425 ካ/ሜ በግቢው የቀበሌ ቤት ያለው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 116,502.39 (አንድ መቶ አስራ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ሁለት ብር ከሰላሳ ዘጠኝ ሣንቲም) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 28 ቀን 2016 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ9፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናት ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመወሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ዳ/ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት የፍ/አ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት
