የቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አላቂ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች ፣ የተሽከርካሪ የጥገና የእጅ ዋጋ (ጋራዥ) እና ልዩ ልዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
በአብክመ ደ/ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር-ቃ/ወ/ግ/ጨ/001/2017
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግን/አስ ቡድን ለቃሉወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት -ı አላቂ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች
- ሎት 2 የተለያዩ የመኪና ጎማዎች
- ሎት 3 የተሽከርካሪ የጥገና የእጅ ዋጋ (ጋራዥ) እና
- ሎት 4- ልዩ ልዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- ተጫራቾች ህጋዊ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ቲን ነምበር ያላቸው። መረጃ ኦርጂናል እናየማይመለስ ኮፒ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ ሲኖርበትየግዥው መጠን ከብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚፈለገውን የእቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሚያቀርቡት ዋጋ ከነቫቱ ነው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ25/11/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 9/12/2016 ዓ/ም 11፡00 ሰዓትድረስ ቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.9 በመምጣት የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለትመቶ ብር/ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል / መግዛት ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች ለሎት-1- 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ፣ ለሎት-2 20,000 /ሀያ ሺህ ብር/ ለሎት-3 8,000 /ስምንት ሺህ ብር/ ፣ ለሎት -4 30,000 ብር/ሰላሳ ሺህ/ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተየባንክ ዋስትና የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው። የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ በቢድ ቦንድከሆነ ከ6o ቀን ያነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥለሎት1፣ 2 እና ለሎት 4 10% እንዲሁም ለሎት-3-3% በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክዋስትና የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዋናና ኮፒ በማለት ለየብቻ በፖስታ አሽጎ - ስምና አድራሻውንበመጻፍ ቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥንዘወትር በስራሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻፖስታውን ማስገባት የሚቻል ሲሆን በዚሁ እለት 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይምህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድተቀባይነት የሌለው ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በመክፈቻው እለት የማይገኙ ከሆነጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በአሸነፈበት ዋጋ በፍትህ ጽ/ቤት ቀርቦ ውል ለመውሰድፍቃደኛ የሆነ መሆን አለበት፡፡
- በሎት 4 ላይ የተገለጹትን እቃዎች የአንዱን ዋጋ በመሙላት አመታዊ የኮንትራት ውል የሚወስድ ሲሆንበውሉ መሰረት እቃዎቹን ተቋማት በሚፈልጉት መጠን መሰረት በወረዳችን ንብረት ከፍል ድረስ ለማቅረብፍቃደኛ መሆን ሲኖርበት በሎት 1 እና 2 የተገለጹት እቃዎች በአንድ ጊዜ በጥቅል ንብረት ክፍል የሚገቡመሆኑ መታወቅ አለበት።
- ውድድሩ የሚካሄደው በእያንዳንዱ የሎቶች (ማለትም ሎት 1፤ ሎት 2፤ ሎት 3 እና ሎት 4፤) ለየብቻ ድምርሲሆን አሸናፊው ድርጅት (የሎት 1፤ሎት2 እና ሎት 4) እቃዎችን ቃሉ ወረዳ ንብረት ክፍል ድረስ ማስገባትአለበት፡፡
- ሁሉም የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማ መኖር የሚገባው ሲሆን ስርዝ ድልዝ ሲያጋጥም በፊርማ መረጋገጥይኖርበታል።
- መ/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ከአሸነፈው እቃ ወይም ገንዘብ መጠን ላይ 20% ጨምሮወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ክልሉ ላወጣቸው የግዥ አፈጻጸም መመሪያዎች ተገዥ መሆን ሲኖርባቸው ማሸነፉ ከተነገረበኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራስን ማግለል አይቻልም፡፡
- አሸናፊው ተወዳዳሪ ኦርጂናል እቃዎችን ማቅረቡ ግዴታ ሲሆን ተጫራቾች ሰነድ ሲገዙ ጽ/ቤታችን በሎት1 እና ሎት 2 ለተገለጹት እቃዎች ያዘጋጃቸውን ናሙናዎች በማየት በናሙናው መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጋራዥ ጨረታን በተመለከተ የክልሉ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ በሚያወጣው ዝቅተኛና ከፍተኛ(minimum and maximum) መነሻ ጣሪያ መሰረት የሚሞላ መሆኑ ይታወቅ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ ቃሉ ወረዳ ግዥና ንብረትአስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 551 4657 በመደወልማግኘት ይችላሉ፡፡
በአብክመ ደ/ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን
/ኮምቦልቻ/
