ኢትዮ ዌትላንድስና ናቹራል ሪሶርስ አሶሴሽን (EWNRA) የፍራፍሬ ችግኝ መግዛት ይፈልጋል
Ethio Wetlands and Natural Resources Association (EWNRA)(ኢትዮ ዌትላንድስ ኤንድ ናቹራል ሪሶርስስ አሶሴሽን)
በድጋሜ የወጣ የፍራፍሬ ችግኝ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ዌትላንድስና ናቹራል ሪሶርስ አሶሴሽን (EWNRA) ሀገር በቀል የልማት ድርጅት ሲሆን፤ ማህበረሰብ ተኮርለሆነ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራም የሚዉል የፍራፍሬ ችግኝ ማለትም የዋስ ዝርያ የተዳቀለ (ግርፍትድ) አቮካዶበቁጥር 12,681 እና የኢቲንገር ዝርያ የተዳቀለ ግርፍትድ) አቮካዶ በቁጥር 1,409።
ስለዚህ በፍራፍሬ ችግኝ ማፍላት ሥራ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉአካላት የጨረታዉን ሰነድ ከሃምሌ 25 እስከ ነሀሴ 01፣ 2016 ዓ.ም ባሉት 07 (ሰባት) ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራስዓት አዲስ አበባ ከተማ ከሚገኘው ኢትዮ ዌትላንድስና ናቹራል ሪሶርስ አሶሴሽን (EWNRA) ዋና መስሪያ ቤትእና ኢሉአባቦር ዞን መቱ ከተማ ከሚገኘው ድርጅታችን ጽ/ቤት በመቅረብ በብር 100 (አንድ መቶ) በመግዛትመወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን ተወዳዳሪዎች የጨረታዉን ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግለጨረታ ማስገቢያ ታስቦ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ኢሉአባቦር ዞን መቱ ከተማ ከሚገኘው ድርጅታችን ጽ/ቤትእንዲያስገቡ እያሳሰብን፣ ጨረታው የሚዘጋው ነሀሴ 01፣ 2016 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ሲሆን የጨረታዉ ሳጥንከቀኑ 8፡30-9፡00 ሰዕት ድረስ ታሽጎ ይቆያል። ጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉበተገኙበት በተመሳሳይ እለት ማለትም ነሀሴ 01፣2016 ዓ.ም እለተ እረቡ ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት ኢሉአባቦር ዞንመቱ ከተማ በሚገኘው ድርጅታችን ጽ/ቤት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን።
በጨረታዉ ለመወዳደር መሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች ቅድመ ሁኔታዎች
- በፍራፍሬ፣ ቅመማቅመምና የዛፍ ችግኝ ማፍላት ሥራ ለ2016 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የሙያ ፈቃድ ያለዉ ያላት
- የዘመኑን ግብር የከፈለ
- የተዳቀለ (ግርፍትድ) አቮካዶ ሥራ እውቅና ካለው ስልጠና የወሰደና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ለተዳቀለ (ግራፍትድ) አቮካዶ የሳዮን ምንጭ (sajon source) ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፤
- የተዳቀለ (ግራፍትድ) አቮካዶ ላይ የተከሰተዉን በሽታ መከላከያ ኬሚካል መረጨቱን ከሚመለከተዉግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ጽ/ቤት (ከዞን ወይም ወረዳ) ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- ካሁን በፊት ለሰራባቸዉ ተመሳሳይ ሥራዎች ማለትም የተዳቀለ (ግርፍትድ) አቮካዶ ሥራ ከ3 በላይ ማስረጃማቅረብ የሚችል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታ ከገባበት ጠቅላላ ዋጋ መጠን 10% የሚሆን ሲፒኦ (CPO) በባንክ ማስያዝየሚችል፣
- በድርጅቱ አቅራቢነት የሚገባውን የውል ስምምነት ህጎች የሚያከብርና ጥራቱን የጠበቀ ችግኝ ውልከተገባበት ቀን ጀምሮ ሁለት ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የሚያስረክብ
- ጨረታውን አልፎ ወደ ውል ስምምነት የሚገባ ተጫራች ለቅድመ ክፍያ ዋስትና (Advance guarantee) የሚሆን ለአንድ ወር ጸንቶ የሚቆይ ውል ከገባበት መጠን 30% የሚሆን የባንክ ዋስትና ደብዳቤ ወይምሲፒኦ (CPO) ድርጅቱ በሚያስቀምጥለት የጊዜ ገደብ ውስጥ ማቅረብ ማስያዝ የሚችል፣
- የተዳቀለ (ግርፍትድ) አቮካዶ ችግኝ የተዘጋጀበት ቦታ ከኢሉአባቦር ዞን መቱ ከተማ ከ 100 ኪሎ ሜትር በላይርቀት ካለው ተጫራቾች የአየር መጠበቂያ ትራንስፖርት (Air-conditioned transport) ማቅረብ የሚችሉመሆኑን ታሳቢ በማድረግ የሚቀርበው ችግኝ ዋጋ ኢሉአባቦር ዞን መቱ ከተማ በሚገኘው ድርጅታችን ጽ/ቤት ድረስ የማጓጓዣ ዋጋን ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት።
- ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ አዲስ አበባ ከተማ ከሚገኘው ኢትዮ ዌትላንድስና ናቹራል ሪሶርስ አሶሴሽን(EWAA) ዋና መስሪያ ቤት፣ ኢሉአባቦር ዞን መቱ ከተማ ከሚገኘው ድርጅታችን ጽ/ቤት ወይም ቤንች ሸኮዞን ሚዛን- አማን ከተማ ከሚገኘው ድርጅታችን ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-5527791/047-1411057/047-3350634 ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
ማሳሰቢያ
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀነዉ።
