የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር DCDE 003/2017
ለመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ሀረሪ
ለመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ሀረሪ፣ ለድሬዳዎ፣ ለጅግጅጋ እና ለነቀምት (ለደቡብ ግንባር ሆስፒታል) ዙሪያፕሮጀከት አገልግሎት የሚውሉ ተሽከርካሪ/መኪና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፦
1. ማንኛውም ተጫራች ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፤የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ፣በዘርፉየታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የውጪ አገር ተጫራቾች በሚሆኑበት ጊዜ በተቋቋሙበት አገር የተሰጣቸውን የኩባንያ ምዝገባወረቀት ወይም ፈቃድ ወዘተ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱ በድርጅታችን ፋይናንስ ዴስክመውሰድ ይጠበቅባችኋል፡፡
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በTOR በተያያዘው ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ከተገለፀው ቀንና ሰዓት በፊት በድርጅቱ የግዥ ዴስክ ለዚህ ተብሎበተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
6. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ቅዳሜ፤እሁድ ወይም የህዝብ በአል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀንይተላለፋል፡፡
7. የጨረታ ማስከበሪያ እንደ ተጫራቹ ምርጫ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ(CPO) ብር 15,000.00(አስራ አምስት ሺህ ብር) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
8. ጨረታው ከሐምሌ 14/2016 እስከ ሐምሌ 29/2016 ዓ.ም አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ሐምሌ 29/2016 ዓ.ም ከጧቱ 4፡00ሰዓት የጨረታው ሳጭን ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጧቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱግዥ ዴስክ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ይካሄዳል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአከፋፈት ሂደት ባይገኙምየጨረታው የአከፋፈት ሂደት አያግደውም፡፡
አድራሻ- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 896 06 33/011 896 06 23
አድራሻ ካሳንቺስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጀርባ ከዚህ ቀደም
ስኳር ኮርፖሬሽን የነበረበት የኪያ-ሜድ ኮሴጅ ህንጻ ግራውንድ ላይ
